EthiopiaTech

አዋሽ ባንክ ህገ-ወጥ የገንዘብ ፍሰትን የሚቀንስ ዲጂታል የገንዘብ ማስተላልፊያ አገልግሎት መስጠት ጀምሬያለሁ አለ፡፡

አዋሽ ባንክ ህገ-ወጥ የገንዘብ ፍሰትን የሚቀንስ ዲጂታል የገንዘብ ማስተላልፊያ አገልግሎት መስጠት ጀምሬያለሁ አለ፡፡

ባንኩ ና ወርልድሪሚት ገንዘብ በዲጂታል ማስተላለፍን በጋራ ለመስራት መፈራረማቸውን ዛሬ በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል፡፡
ወርልድ ሪሚት የገንዘብ ማስተላለፊያ ከ 50 በላይ ሀገራትና ከ145 በላይ መዳረሻዎች ላይ እየሰራ መሆኑን እና በ ኢትዮጲያ ውስጥ በወርልድ ሪሚት የተደረገ የገንዘብ ልውውጥ ከ160 በመቶ በላይ እንዳደገ በምስራቅ እና መካከኛው አፍሪካ የወርልድሪሚት ዳይሬክተር ሻሮን ካሪካ ተናግረዋል፡፡
የሚላከው የውጪ ምንዛሪም ከአዎስትራሊያ፣ አሜሪካ፣ እንግሊዝና ካናዳ መሆኑን ሰምተናል፡፡
ዳይሬክተሯ ለአርትስ ቲቪ እንደተናገሩት ሰዎች ዲጂታል አገልግሎትን ሲጠቅሙ ምንም አይነት የማስተላለፊያ ክፍያ አይጠየቁም፤ ተንቀሳቃሽ ስልኮቻቸውን ተጠቅመው መላክ ይችላሉ ብለዋል፡፡
የአዋሽ ባንክ ሆል ሴል ቺፍ ኦፊሰር አቶ ታደሰ ገመዳ በበኩላቸው የገንዘብ ማስተላለፊያ መንገዱ ዲጂታል በመሆኑ ልፋትን እና ጊዜን የሚቆጥብ ነው ፤በተጨማሪም ህገ-ወጥ የገንዘብ ፍሰትን በከፍተኛ ደረጃ የሚቀንስ በመሆኑ መንግስት የጀመረውን ህገ-ወጥ ገንዘብ ማስተላለፍን የመከላከል እንቅስቃሴ የሚደግፍ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button