Ethiopia

በአማራ ክልል የሚገኙ ዩንቨርስቲዎች የጣና ሃይቅን ለመታደግ በህብረት እየሰሩ መሆናቸውን አስታወቁ

አዲስ አበባ፣ሐምሌ22፣ 2012 በአማራ ክልል የሚገኙ 10ሩም ዩንቨርስቲዎች የጣናን ሃይቅ ለመታደግ በርካታ የምርምር እና የጥናት ስራዎችን መስራታቸውን ለአርትስ ቲቪ ገልፀዋል፡፡ዩንቨርስቲዎቹ በማህበረሰብ አገልግሎት ፤ በሰላም ግንባታና በእሴት ግንባታ ላይ ከመማር ማስተማሩ ጎን ለጎን እየሰሩ መሆናቸውም ነው የገለፁት ፡፡በተለይም በክልሉ የሚገኘውን የጣና ሃይቅ ለመታደግ በርካታ አማራጮች እና ሙከራዎች መደረጋቸውን የወሎ ዩንቨርስቲ ፕሬዚዳንት እና የአማራ ዩንቨርስቲዎች ሰብሳቢ ዶክተር አባተ ጌታሁን ገልፀዋል፡፡በክልሉ የሚገኙ የውሃ አካላት ላይ ችግሮች መኖራቸውን የገለፁልን ሃለፊው በተለይ የአባይ ውሃ ከጣና እንደመውጣቱ በሃይቁ የተንሰራፋው የእንቦጭ አረም ችግር ከማስከተሉ በፊት በርካታ አካለት የድርሻቸውን ርብርብ እያደረጉ መሆናቸውን ነው ያነሱት፡፡በክልሉ በሚገኙ ዩንቨርስቲዎች የተለያዩ የምርምርና የጥናት ስራዎች የአባይና መሰል የውሃ አካላት ፤ ህብረተሰቡ ሊጠቀምባቸው የሚችልባቸውን መንገዶች ማመንጨት መቻል እንዳለባቸውም ተገልጿል፡፡እንደ ዶክተር አባተ ገለፃ ችግሩን ከስር መሰረቱ ለመታደግ በርካታ ስራዎች መሰራት እንዳለባቸው በመጠቆም በስርዓተ ትምህርቱ ውስጥ የሀገር እሴቶች በማካተት ታዳጊዎችን ማብቃት እንደሚገባ ነው በመልዕክታቸው የገለጹት ፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button