EthiopiaPoliticsRegionsSocial

ዛሬ በተፈጠረው የፀጥታ ችግር ምክያትን በጀዋር መሃመድ የሚመራዉ ቡድን የኦሮሚያ የሚያደርገውን ጉብኝቱን ለጊዜው ማቆሙን ኦ ኤም ኤን ዘገበ።

በዛሬዉ ዕለት በሻሸመኔ ከተማ በተፈጠረ መገፋፋትና መረጋገጥ የ3 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ በርከት ያሉ ሰዎች ላይ ደግሞ የአካል ጉዳት መድረሱን አቶ አዲሱ አረጋ የኦህዴድ የገጠር ፖለቲካ አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አስታውቀዋል።
አደጋው የደረሰው የኦሮሚያ ሚዲያ ኔትዎርክ ዳይሬክተር አቶ ጃዋር መሃመድ እና ሌሎች የቡድኑ አባላት አቀባበል ለማድረግ በከተማዋ በተዘጋጀ ስነ ስርዓት ላይ ነዉ።

በአደጋውም እስካሁን የ3 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ በርካቶች ላይ ደግሞ የተለያየ መጠን ያለው ጉዳት መድረሱም ታዉቋል። በአቀባበል ስነ ስርዓቱ ላይ በተፈጠረ መገፋፋትና መረጋገጥ በደረሰው አደጋ ህይወታቸው ላለፈ እና ጉዳት ለደረሰባቸው ዜጎች የተሰማንን ጥልቅ ሀዘን እንገልፃለን። ለወዳጅ ዘመዶቻቸዉም መፅናናትን እንመኛለን ብለዋል አቶ አዲሱ።

ከአደጋው ጋር ተያይዞም የተወሰኑ ህገወጥ ቡድኖች ከተማዋ ላይ ህገወጥነት፣ ብጥብጥ እና ግጭት ለማስነሳት ተንቀሳቅሰዋል። በዚህ ሂደትም ቦንብ ይዞ ተገኝቷል በሚል ሀሰተኛ ወሬ በአንድ ግለሰብ ላይ በቡድን ጥቃት በማድረስ የግለስቡ ህይወት ሊያልፍ ችሏል። ይህ አስነዋሪና ጭካኔ የተሞላበት ድርጊት ሰላም ወዳዱን የሻሸመኔ ከተማ ህዝብም ሆነ የሻሸመኔን ቄሮ የማይወክል የክፋት ተግባር ነዉ። ግለሰቡ ላይ የተፈፀመዉን ግድያም አጥብቀን እናወግዛለን ብለዋል። በተጨማሪም አንድ የሻሸመኔ ከተማ የፀጥታና አስተዳደር ፅህፈት ቤት ተሽከርካሪ በእሳት ጋይቷል። ተሽከርካሪው የተቃጠለዉ ፀጥታ የማስከበበር ስራ ላይ በተሰማራበት ወቅት ቦምብ ጭኗል በሚል የተሳሳተ መረጃ በመሰራጨቱ ነዉ። ሆኖም ግን በተሽከርካሪው ላይ ምንም አይነት ቦምብ እንዳልነበረ ከኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ማረጋገጥ ተችሏል ብለዋል አቶ አዲሱ።

በአሁኑ ወቅት ሰላም ወዳዱ የሻሸመኔ ከተማ ህዝብ ከፀጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት ባደረጉት ጥረት ከተማዋ ወደ መረጋጋት ተመልሳለች። በዛሬዉ ዕለት በተፈጠረዉ ችግር በመሳተፍ የተጠረጠሩ ግለሰቦችንም ህዝቡ እና ፖሊስ በመቀናጀት በህግ ቁጥጥር ስር እንዲዉሉ በማድረግ ላይ ይገኛሉ ተብሏል።

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button