AfricaPolitics

ህንድ በአፍሪካ 18 ኢምባሲዎችን ልትከፍት ነው፡፡

ህንድ በአፍሪካ 18 ኢምባሲዎችን ልትከፍት ነው፡፡
የህንዱ ጠቅላይ ሚንስትር ናሬንድራ ሞዲ ሰሞኑን ዩጋንዳ ካምፓላ ነበሩ፡፡ ከሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ዩዌሬ ሙሴቬኔ ጋር ባደረጉት ውይይት ህንድ ከመላው አፍሪካ ጋር በትብብር የመስራት ከፍተኛ ፍላጎት እንዳላት ገልጸዋል፡፡
ሞዲ ለዩጋንዳ ፓርላማ ባደረጉት ንግግር ታላቁ የነጻነት ታጋይ ማህተመ ጋንዲ አፍሪካ በባርነት እየኖረች የህንድ ነጻ መውጣት ጎዶሎ ነው የሚል አቋም ነበራቸው ብለዋል፡፡
ዛሬ ሁላችንም ነጻ ሀገሮች ነን እናም አብረን ሰርተን በጋራ እናድጋለን በማለትም የህንድና የአፍሪካን ግንኙነት የማጠናከር ጽኑ ፍላጎት እንዳላቸው አብራርተዋል፡፡
ዘገባው የሲ ኤን ኤን ነው፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button