COVID-19HealthNewsኢትዮጵያ

በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰአታት የኮሮናቫይረስ የተገኘበት ሰው የለም::

በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰአታት የኮሮናቫይረስ የተገኘበት ሰው የለም:: ተባለ በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰአታት ውስጥ በተደረገ ምርመራ የኮሮናቫይረስ የተገኘበት ሰው አለመኖሩን የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ አስታውቀዋል፡፡ በ24 ሰአታት ውስጥ ለ965 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ምርመራ መደረጉን ነው የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ አስታወቁት። ሚኒስትሯ በ24 ሰአታት ውስጥ በተደረገው ምርመራም ቫይረሱ የተገኘበት ሰው
አለመኖሩንም አስታውቀዋል። በአጠቃላይ በኢትዮጵያ የኮሮናቫይረስ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 116 ሲሆን፥
ከእነዚህም ውስጥ 90 ሰዎች በለይቶ ህክምና ላይ እንደሚገኙና ፤ 21 ሰዎች ደግሞ
ከቫይረሱ ማገገማቸው ይታወቃል። ዛሬ በተደረገው ምርመራ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች አለመገኘታቸው የዛሬን እንጂ
የመጭዎቹን ቀናት ውጤት ስለማይገልፅ ህዝቡ ማዘናጋት እነዳያይም ደዶክተር ሊያ አሳስበዋል፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button