EconomyEthiopiaPolitics

የኢትዮጲያ ገቢዎች እና ጉምሩክ ባለስልጣን በ2011 ሩብ አመት 25 ቢሊዮን ብር በላይ ሰብስቤያለው አለ፡፡

የኢትዮጲያ ገቢዎች እና ጉምሩክ ባለስልጣን በ2011 ሩብ አመት ከሃገር ውስጥ ታከስ 25.6 ቢሊዮን
ብር መሰብሰቡን አስታውቋል፡፡
ባለስልጣኑ በሩብ አመቱ 28.3 ቢሊዮን ብር አቅዶ የሰበሰበው ግን 25.6 ቢሊዮን ብር መሆኑን እና
ያልተሰበሰበ 3.2 ቢሊዮን ብር መኖሩን በገቢዎች እና ጉምሩክ ባለስልጣን የሀገር ውስጥ ታክስ ዘርፍ
ምክትል ዳይሬክተር ወ/ሮ ነፃነት አበራ ተናግረዋል፡፡
ምክትል ዳይሬክተሯ የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ቀልጣፋ አሰራር ጉድለት፣ የግብር ከፋይ ነጋዴዎች
ደረሰኝ አጠቃቀም ጉለት ፣የአሰራር አለመዘመን እና የህግ ክፍተቶች የታቀደውን ያህል ገቢ
እንዳይሰበሰብ አድርጓል ብለዋል፡፡
ባለስልጣን መስሪያቤቱ በ2011 በጀት አመት አጠቃላይ ከሃገር ውስጥ ታክስ እና ከውጭ ቀረጥ 2
መቶ 41 ነጥብ ዘጠኝ ቢሊዮን ብር ለመሰብሰብ አቅዷል፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button