loading
የነልደቱ አያሌዉ ኢዴፓ ፈረሰ፡፡

የነልደቱ አያሌዉ ኢዴፓ ፈረሰ፡፡
ፓርቲዉ ከ1አመት ከ8 ወር በፊት በቀድሞ የኢዴፓ ፕሬዝደንት ዶክተር ጫኔ ከበደ በፓርቲዉ ላይ በከፈቱት ክስ ምክንያት ፤በብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ምስክርነት ፓርቲዉ በፍርድቤት እንዲፈርስ ተወስኖ እንደነበር አቶ ልደቱ አያሌዉ ለአርትስ ቲቪ ተናግረዋል፡:
ሆኖም እንደ አቶ ልደቱ ገለጻ ፍርድቤቱ ያሳለፈዉን ዉሳኔ ለማስቀልበስ አስከ ቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ድረስ አቤቱታ ብናቀርብም ምላሽ ሳናገኝ ቀርተናል ብለዉናል፡፡
አሁንም ለጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ አቤቱታችንን አቅርበናል እስካሁን ምላሽ ስላላገኘን መጨረሻችን ወደ መፍረስ እያመራ ነዉ ብለዋል፡፡
አቶ ልደቱ ጉዳዩን በተመለከተ እሁድ 4 ሰዓት መግለጫ እንሰጣለን ብለዋል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *