SportSports

የእንግሊዙ ማንችስተር ሲቲ ባለፉት ስምንት አመታት ለዝውውር ከአውሮፓ ታላላቅ ቡድኖች ከፍተኛውን ገንዘብ አውጥቷል፡፡

አርትስ ስፖርት 01/13/2010
የትኛው ቡድን በሊጉ ቀዳሚ ለመሆን በተጫዋቾች ዝውውወር ከፍተኛ ገንዘብ ፈሰስ አደረገ?
በአውሮፓ የሚገኝ ቡድን በሊጉ የበላይ ለመሆን ምን ያህል ገንዘብ ማውጣት አለበት?
በአሁኑ ጊዜ ባለፉት ስምንት አመታት በዘመናዊ የእግር ኳስ እንቅስቃሴ ውስጥ ለተጫዋቾች ዝውውር ብቻ አራት ክለቦች ከአንድ ቢሊዮን ፓውንድ በላይ አውጥተዋል፡፡
ባለፉት ሁለት የክረምት ተጫዋቾች የዝውውር መስኮት ሁለት ከፍተኛ ዝውወሮች ሲፈፀሙ አስተውለናል፤ የፈረንሳዩ ክለብ ፒ.ኤስ.ጂ ለኔይማር እና ክልያን ምባፔ፤ ለባርሴሎና እና ሞናኮ ተጫዋቾቹን የግሉ ለማድረግ 200 እና 166 ሚሊዮን ፓውንዶችን ወጭ አድርጓል፡፡
የስፔኑ ባርሴሎና ደግሞ ለፊሊፔ ኮቲንሆ እና ኦስማን ዴምቤሌ ባለፉት 12 ወራት ብቻ በድምሩ 281 ሚሊዮን ፓውንድ ፈሰስ አድርጓል፡፡
CIES የተሰኘው የእግር ኳስ ቁጥራዊ መረጃዎችን የሚያወጣ አካል ባለፉት ስምንት አመታት ከፍተኛ ወጭ ያደረጉ ቡድኖችን ዝርዝር ይፋ አድርጓል፡፡
በዚህም መሰረት፡-
1. ማንችስተር ሲቲ ከ2010 ጀምሮ ለዝውውር 1.325 ቢሊዮን ፓውንድ
2. ቼልሲ 1.310 ቢሊዮን ፓውንድ
3. ባርሴሎና 1.258 ቢሊዮን ፓውንድ
4. ፒ.ኤስ.ጂ 1.120 ቢሊዮን ፓውንድ
5. ማንችስተር ዩናይትድ 993.45 ሚሊዮን ፓውንድ
6. ዩቬንቱስ በ978.12 ሚሊዮን ፓውንድ
7. ሊቨርፑል 965.50 ሚሊዮን ፓውንድ
8. ሪያል ማድሪድ 822.16 ሚሊዮን ፓውንድ
9. ሮማ 729.31 ሚሊዮን ፓውንድ
10. አትሌቲከ ማድሪድ በ688.74 ሚሊዮን ፓውንድ ወጭ በማድረግ ተቀምጠዋል፡፡
በመረጃው ኢንተርሚላን፣ ሞናኮ፣ ኤስ ሚላን፣ አርሰናል፣ ኢቨርተን፣ ቶተንሀም፣ ናፖሊ፣ ቫሌንሲያ፣ ባየር ሙኒክ አና ቦሪሲያ ዶርትሙንድ፤ ደግሞ እስከ 11-20 ያለውን ደረጃ መያዝ ችለዋል፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button