AfricaEthiopiaSport

ነገ በሚካሄደው የበርሊን ማራቶን ጥሩነሽ ዲባባ ትካፈላለች

አርትስ ስፖርት 05/01/2011
በIAAF የወርቅ ደረጃ የሚሰጠው የBMW 46ኛው የበርሊን ማራቶን ውድድር ነገ ሲደረግ በሴቶች በሚካሄደው ርቀት ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ጥሩነሽ ዲባባ ተሳታፊ እንደምትሆን ተረጋግጧል፡፡
ጥሩነሽ በማራቶን ርቀት የበርሊኑ አራተኛዋ ውድድር ሲሆን የግሏ ምርጥ ሰዓት ደግሞ ለንደን ላይ ያስመዘገበችው 2፡17፡56 ነው፡፡ በውድድሩ ከ2 ስዓት ከ20 ደቂቃ በታች ያላቸው አራት አትሌቶች የሚካፈሉ ሲሆን ጥሩነሽን ጨምሮ የባለፈው አመት የበርሊን ማራቶን አሸናፊ ኬንያዊቷ ግላዲስ ቼሮኖ (2፡19፡25)፤ ኢትዮጵያዊቷ አሰለፈች መርጊያ (2፡19፡31)፤ እንዲሁም የአለም ሻምፒዮን ጥምር አሸናፊ ሌላኛዋ ኬንያዊት ኢድና ኪፕላጋት (2፡19፡50) ብርቱ ፉክክር ያካሂዳሉ ተብሎ ይጠበቃሉ፡፡
በባለፈው አመት የበርሊን ማራቶን 2ኛ ደረጃ በመያዝ ያጠናቀቀችው ኢትዮጵያዊቷ ሩቲ አጋ (2፡20፡41) እና ጃፓናዊቷ ሚዙኪ ማትሱዳ (2፡22፡44) በውድድሩ ቀላል ግምት የሚሰጣቸው አትሌቶች አይደሉም ተብሏል ፡፡
ጥሩነሽ ስለ ውድድሩ አስተያየቷን የሰጠች ሲሆን ‹‹ለውድድሩ በጣም ተዘጋጅቻለሁ፤ በእሁዱ ውድድር የግሌን ምርጥ ስዓት ለማሻሻል እፈልጋለሁ›› ስትል ተናግራለች፡፡
በወንዶች የኦሎምፒክ ሻምፒዮኑ ኬንያዊው ኢሉይድ ኪፕቾጌ (2፡03፡05) እና የሀገሩ ልጅ የቀድሞ የአለም የማራቶን ክብረወሰን ባለቤት ዊልሰን ኪፕሳንግ (2፡03፡13) እንዲሁም ኤርትራዊው ዘረሰናይ ታደሰ (2፡10፡41) ከተወዳዳሪዎች መካከል የተሻለ የአሸናፊነት ግምት ተሰጥቷቸዋል፡፡
በውድድሩ ከ133 ሀገራት የተወጣጡ ከ44ሺ በላይ ሯጮች ይካፈላሉ ተብሏል፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button