EthiopiaSocial

“እውነት ነው ከ3 ሚሊዮን ብር በላይ ተሰብስቧል ነገር ግን እኛ የምንሰርቅ ሰዎች አይደለንም፡፡”

“እውነት ነው ከ3 ሚሊዮን ብር በላይ ተሰብስቧል ነገር ግን እኛ የምንሰርቅ ሰዎች አይደለንም፡፡”
ይህንን ያለዉ አርቲስት ቴዎድሮስ ተሾመ ነዉ፡፡

ለአንጋፋው አርቲስት ፍቃዱ ተክለማርያም ህክምና የሚውል ከ 3 ሚሊዮን ብር በላይ ኮሚቴዎቹ እጅ ላይ ነው የሚሉ እና ወደ ኮሚቴዎቹ ጣት የሚቀስሩ ፅሁፎች በማህበራዊ ድረገፆች መውጣታቸውን ተከትሎ አርትስ ቲቪ ከኮሚቴዎቹ አንዱ የሆነውን አርቲስት ቴዎድሮስ ተሾመን አነጋግሯል፡፡
ቴዎድሮስ ተሾመ ለአርትስ እንደገለፀው ለህክምና ከተሰበሰበው ገንዘብ ላይ ለአርቲስቱ የቀብር ስነ -ስርዓት ማስፈፀሚያ የወጣ ሲሆን አሁንም በገንዘቡ ታላቅ የኪነጥበብ ሰው ነው እና ትውልድ ሊጎበኘው የሚችል ሃውልት ይሰራለታል ተዝካሩም ክብሩን በሚመጥን መልኩ እንዲወጣ እንደሚያደርጉ ተናግሯል ፡፡
በወቅቱ ገንዘቡ “go fund me” በሚል ዌብሳይት እንዲሁም በሌሎችም የገንዘብ ማሰባሰቢያ መንገዶች የተሰበሰበ ሲሆን አርቲስቱ ከተሰበሰበው ገንዘብ ላይ ለወጣቷ የኩላሊት ታማሚ ሁለት መቶ ሺህ ብር ሰጥቷታል ፡፡
ከእነዚህ ወጪዎች የሚተርፈውን ገንዘብ ምን ላይ እንደሚውል የተወሰነ ነገር ባይኖርም ሁለት አማራጮች እንደሚኖሩ እና እነዚህም አማራጮች የተረፈውን ገንዘብ በህግ አግባብ ህጋዊ ለሆነ ወራሽ ለመስጠት አልያም ለህዝብ የሚመለስበትን አግባብ መፈለግ እንደሚሆን ነው ቴዎድሮስ ለጣቢያችን የገለፀው፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button