Ethiopia

ኢትዮ ቴሌኮም የኢንፎርሜሽን ቴከኖሎጂ እና የኔትወርክ መሰረተ ልማትን የሚያፋጥን ዘመናዊ የሞጁላር መረጃ ማእከል ስራ አስጀመረ።

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 14፣ 2013 ኢትዮ ቴሌኮም የኢንፎርሜሽን ቴከኖሎጂ እና የኔትወርክ መሰረተ ልማትን የሚያፋጥን ዘመናዊ የሞጁላር መረጃ ማእከል ስራ አስጀመረ። ይህ ዘመናዊ የሞጁላር መረጃ ማእከል በከፍተኛ ደረጃ የሃይል ፍጆታን የሚቀንስ፣ በቀላሉ ፍላጎትን ተከትሎ ሊስፋፋ የሚችል እና ፈጣን የሲስተም ተከላ ለማድረግ የሚያስችል ነው ተብሏል፡፡ የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈጻሚ ፍሬህይወት ታምሩ በኢትዮጵያ ከጊዜ ወደጊዜ እየጨመረ ያለውን
የግል እና የመንግስት ተቋማት የመረጃ ክምችት እና ስርጭት ለማዘመን ጥራቱን የጠበቀ የመረጃ ማእከል መገንባት አስፈላጊ ነው ብለዋል።

ኩባንያው ባደረገው መጠነ ሰፊ እንቅስቀሴ ደንበኞቹን 426 በመቶ ለማሳደግ እንደተቻለ ገልጸው ይህን መሰረት አድርጎ ማዕከሉ እንደተሰራም ተናግረዋል
ማእከሉ ኩባንያው ለሚሰጠው  ለሁሉም የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂና የኔትወርክ መሰረተ ልማቶች አገልግሎት እንዲሰጥ ታስቦ የተዘጋጀ መሆኑንም ጠቁመዋል። ኩባንያው የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች በፍጥነት ተደራሽ እንዲሆኑ እንዲሁም የሀይልና ፍጆታው ያነሰና

ለጥገና የሚወጣውን ወጪ 35 በመቶ እንደሚቀንስም ገልጸዋል። በቅርቡ የተዋወቀው ቴሌ ብር የተሰኘው አገልግሎትም በዚሁ ማእከል ምክንያት ለስራ ይበቃል ነው ያሉት ዋና ስራ አስፈጻሚ። ግንባታውን ለማጠናቀቅ ሁለት ወራት እንደፈጀና ለዚህም 3 ነጥብ 5 ሚሊየን ዶላር ወጪ እንደተደረገበት ኩባንያው ለአርትስ በላከው መግለጫ አስታውቋል፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button