Ethiopia

በጦርነቱ ጉዳት ለደረሰባቸው የማኅበረሰብ ክፍሎች የተለያዩ የሕክምና ድጋፎች ለመስጠት አንድ መቶ በጎ ፍቃደኛ የጤና ባለሙያዎች ወደ አማራ ክልል አቀኑ።

አዲስ አበባ፣ ጥር 23፣ 2014 በጦርነቱ ጉዳት ለደረሰባቸው የማኅበረሰብ ክፍሎች የተለያዩ የሕክምና ድጋፎች ለመስጠት አንድ መቶ በጎ ፍቃደኛ የጤና ባለሙያዎች ወደ አማራ ክልል አቀኑ። የሕክምና ባለሙያዎቹ ከጥር 22 እስከ 29 ቀን 2014 ዓ.ም በአማራ ክልል የሕክምና ምርመራ፣ ሕክምናና የምክር አገልግሎት ይሰጣሉ፤ መድኃኒትም ያቀርባሉ ተብሏል።

በጎ ፍቃደኞቹ የሕክምና ድጋፋቸውን የሚሰጡባቸው የአማራ ክልል ከተሞች ሸዋሮቢት፣ ኮምቦልቻ፣ ደሴ፣ ሐይቅ፣ ባቲ፣ ኩታበር፣ ቆቦና ወልድያ ናቸው።       
የበጎ ፍቃደኞቹ ቡድን በጅማ ዩኒቨርሲቲ የምረቃ ተማሪዎች ኅብረት አስተባባሪነት ከተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች የተውጣጡ የሕክምና ባለሙያዎችን ያቀፈ ነው።   
ኮምፓሽን ኢንተርናሽናልም የበጎ ፍቃድ አገልግሎቱን በማስተባበር የተሳተፈ ሲሆን ሰን ራይዝ ዴቨሎፕመንት ኢትዮጵያም የዚሁ መልካም ስራ አጋር ነው ተብሏል፡፡


በጎ ፍቃደኞቹ በጦርነቱ ለተጎዱ የማኅበረሰብ ክፍሎች ከሕክምና ድጋፍ ባሻገር የምክርና የሥነ-ልቦና ድጋፍ ላይ ትኩረት አድርገው እንደሚሰሩም ተነግሯል፡፡
ለእነዚህ የማኅበረሰብ ክፍሎች ድጋፍ ማድረግ የተጎጂዎቹን ሥነ-ልቦና በመመለስ ወደ ቀደመ ሕይወታቸው እንዲመለሱ ለማድረግ ትልቅ መነሳሳት እንደሚፈጥርላቸው በጎ ፍቃደኞቹ ተናግረዋል፡፡ በጎ ፍቃደኞቹ በጤናው ዘርፍም ይሁን በሌሎችም የሙያ መስኮች ያሉ ወጣቶች ወደ ሥፍራው በማቅናት ሠብዓዊ ድጋፍ እንዲያደርጉም ጥሪ አቅርበዋል።

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button