EthiopiaLegalPoliticsSocial

ከ40 በላይ የሜቴክና የደኅንነት አባላት በቁጥጥር ሥር ዋሉ

አርትስ 01/02/2011

ከ40 በላይ የሚሆኑ የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (ሜቴክ) ከፍተኛአመራሮችና የደኅንነት አባላት በቁጥጥር ሥር መዋላቸው ተጠቁሟል፡፡

የሜቴክ ከፍተኛ አመራሮችና የደኅንነት አባላት ትናንትና ጥቅምት 30 ቀን 2011 ዓ.ም. ለስብሰባ ከተጠሩበት ስፍራ በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን የሪፖርተርምንጮቼ ነገረኝ ብሎ ዘግቧል፡፡

እንደ ምንጮቹ ገለጻ፣ ከፍተኛ አመራሩና የደኅንነት አባላት በቁጥጥር ሥር የዋሉትገርጂ አካባቢ በሚገኘውና ቀድሞ ኢምፔሪያል ሆቴል ተብሎ ይጠራ በነበረውናአሁን የኮርፖሬሽኑ ንብረት በሆነው አሞራው ሕንፃ ውስጥ መሆኑ ተገልጿል፡፡

አመራሮቹ በቁጥጥር ሥር የዋሉበት ምክንያት ባይገለጽም፣ የፌዴራል ፖሊስጌዜያዊ እስር ቤት በሆነው በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ማቆያ ቤት መታሰራቸውንምንጮቹ አክለዋል፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button