AfricaEthiopiaSocial

ዓለም አቀፍ የሴቶች እና ወጣቶች የሰላም ኮንፍረንስ በአዲስ አበባ ተካሄደ

የሰላም ኮንፍረንሱ የተካሄደው በአዲስ አበባ የኢሲኤ አዳራሽ ነው፡፡
አለም አቀፍ የሴቶችና ወጣቶች የሰላም ኮንፈረንስ ላይም የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስ፣ የቀድሞ የኢፌዴሪ ፕሬዝደንት ዶር ነጋሶ ጊዳዳ፣ የኦሮሚያ ሚዲያ ኔትዎርክ ዋና ዳይሬክተር አቶ ጃዋር መሃመድ እና ሌሎች ተጋባዥ እንግዶች ስለሰላም የሚያወሳ አጫጭር ጹሁፎችን አቅርበዋል።
ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ ዳግማዊት ሴቶች እና ወጣቶች ለሰላም መረጋገጥ ትልቅ ሚና ሲጫወቱ እንደቆዩና አሁንም የጎላ ሚና እንዳላቸው ገልጸው ወጣቶች ልማትን ለማረጋገጥ በሚደረገው እንቅስቃሴ ውስጥ ቁልፍ ድርሻ እንደሚጫወቱ መንግስት በጽኑ ያምናል ብለዋል።
በዝግጅቱ ላይ ከተለያዩ የሀገሪቱ ዩኒቨርስቲዎች የተወከሉ ወጣቶችና ሴቶች መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት ተወካዮችና ምሁራኖችም ተሳትፈዋል።ከአዲስ አበባ ከንቲባ ጽሕፈት ቤት ድረ ገፅ እንዳገኘነዉ፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button