EconomyEthiopiaPolitics

ከስድስት ወራት በኋላ የሁሉም የስኳር ፕሮጀክቶች ግንባታ እንደሚጠናቀቅ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ተናገሩ፡፡

ዶክተር አብይ ይህንን ያሉት በባህርዳር ከተማ ከብአዴን አመራሮች ጋር ባደረጉት ምክክር ላይ ነው፡፡
ባለፉት 9 ወራት የተሻለ ብሔራዊ መግባባትን ለመፍጠርና ኢኮኖሚያዊ ለውጦችን ለማምጣት ውጤታማ ተግባራት ተከናዉነዋል ብለዋል፡፡
በሀገሪቱ የተሻለ መግባባት ለመፍጠርም ከዲያስፖራው ማህበረሰብ ጋር የነበረውን ግንኙነት የማስተካከልና በሀይማኖቶች ውስጥ የነበረውን መከፋፈል የማጥፋት ስኬታማ ስራዎች ተሰርተዋል ብለዋል፡፡
በኢኮኖሚ ረገድም የውጭ ምንዛሬ በቤታቸው ያከማቹ ዜጐች ወደ ባንክ እንዲያስገቡ በተጠየቀው መሠረት በሁለት ሳምንታት ብቻ እስከ 130 ሚሊየን ዶላር በባንኮች ተመንዝሯል ብለዋል፡፡ ግንባታቸው በተለያዩ ምክንያቶች ተጓቶ የነበሩ የስኳር ፕሮጀክቶችም አሁን ላይ የማጠናቀቂያ ስራ እየተሰራ መሆኑንና ከስድስት ወራት በኋላ ሁሉም የስኳር ፕሮጀክቶች እንደሚጠናቀቁም ገልፀዋል፡፡
በአጭር ጊዜ ውስጥ የመጡት መልካም ለውጦች የበለጠ ተጠናክረው እንዲቀጥሉም ትክክለኛ የአመራር ስልትን ለመተግበር አመራሮች ሀላፊነታቸውን ሊወጡ ይገባል ብለዋል፡፡
ምንጭ የአማራ መገናኛ ብዙሃን፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button