AfricaEthiopia

በአብዬ የሚገኘው የኢትጵያ የሰላም አስከባሪ ኃይል የቆይታ ጊዜ ተራዘመ

አርትስ 07/03/2011
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት በአብዬ የሚገኘው የሰላም አስከባሪ ኃይል የቆይታ
ጊዜ እንዲራዘም መወሰኑን አስታዉቋል፡፡
የጸጥታው ምክር ቤት በጉዳዩ ላይ ውሳኔውን ያሳለፈው ትናንት ባደረገው ስብስባ ነው ተብሏል፡፡
በተመድ የሱዳን እና የደቡብ ሱዳን ቋሚ መልዕክተኞች በጉዳዩ ዙሪያ ንግግር አድርገዋል፡፡
በዚህም ኢትዮጵያ በአብዬ ሰላምና መረጋጋት እንዲፈጠር እያበረከተችው ላለው ጉልህ አስተዋጽዖ
ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡
በአብዬ የተሰማራው የኢትዮጵያ የሰላም አስከባሪ ኃይል የአካባቢው ማህበረሰብ በሰላም ወጥቶ
እንዲገባ በማድረግ በኩል የላቀ አስተዋጽዖ በማበርከት ላይ እንደሚገኝም መግለጻቸውን የውጭ ጉዳይ
ሚኒስቴር አስታዉቋል፡፡
አብዬ ግዛት ደቡብ ሱዳንና ሰሜን ሱዳን የይገባኛል ጥያቄ የሚያነሱበት ስፍራ መሆኑ ይታወቃል፡፡
በአሁኑ ወቅት በተልዕኮ ላይ 50 የፖሊስ አባላትን ጨምሮ 5 ሺህ 326 ወታደሮች ተሰማርተዋል፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button