COVID-19EthiopiaHealthNewsኢትዮጵያ

ከኮቪድ-19 ታማሚ እናት የተወለደው ሕፃን ከኮሮናቫይረስ ነፃ ሆነ::

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 17፣ 2012 ከኮቪድ-19 ታማሚ እናት የተወለደው ሕፃን ከኮሮናቫይረስ ነፃ ሆነ::
በኤካ ኮተቤ ሆስፒታል ከኮቪድ-19 ታማሚ እናት የተወለደው ሕፃን ከኮሮናቫይረስ ነፃ ሆኗል።በኤካ ኮተቤ ሆስፒታል የለይቶ ሕክምና ማእከል ውስጥ ክትትል እየተደረገላት ከምትገኝ የ34 ዓመት እናት ግንቦት 14 ቀን 2012 ዓ.ም የተወለደው ሕፃን 3.1 ኪ.ግ. ክብደት ያለው ወንድ ልጅ መሆኑም ታውቋል።ከሕፃኑ በተወሰደው ናሙና ላይ በተካሔደው የላብራቶሪ ምርመራ የኮሮናቫይረስ እንደሌለበት ማረጋገጥ ተችሏል።የኮቪድ-19 በሽታ በእርግዝና ወቅት ከእናት ወደ ልጅ እንደሚተላለፍ ለማወቅ የተደረጉ ብዙ ጥናቶች ባይኖሩም፣ እስካሁን ባለው መረጃ ከእናት ወደ ልጅ የመተላለፍ ዕድሉ በጣም አነስተኛ መሆኑም ተገልጿል::የኮሮናቫይረስ በእርግዝና እና ወሊድ ወቅት ከእናት ወደ ልጅ የመተላለፍ ዕድሉ ዝቅተኛ ቢሆንም፣ ከወሊድ በኋላ በጡት ማጥባት ወቅት እና ዘወትር በሚኖር ንክኪ የመተላለፍ ዕድሉ ከፍተኛ ስለሆነ አስፈላጊውን ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባም ተጠቁሟል።እናቶች በእርግዝና ወቅት የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን ለመከላከል ሁሉንም የመከላከያ መንገዶችን አጥብቀው መተግበር፣ የተመጣጠነ ምግብ መመገብ፣ በቂ እረፍት መውሰድ፣ የእርግዝና ክትትል ማድረግ እንዲሁም በጤና ተቋማት መውለድ ብሎም ከጤና ባለሞያዎች የሚሰጣቸውን ምክር በአግባቡ እንዲተገብሩ የጤና ሚኒስቴር አሳስቧል።

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button