Ethiopia

ኢትዮ ቴሌኮም ባለፉት ስድስት ወራት 28 ቢሊዮን ብር ገቢ ማግኘቱን ይፋ አደረገ።

አዲስ አበባ፣ ጥር 23፣ 2014 የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈጻሚ ፍሬህይወት ታምሩ የ2014 በጀት ዓመት የተቋሙን የ6 የስራ አፈፃፀም በማስመልከት መግለጫ ሰጥተዋል። በመግለጫቸውም በ6 ወራት ብቻ ከቴሌኮም አገልግሎት 28 ቢሊዮን ብር ገቢ ማግኘቱን ገልጸዋል።ተቋሙ በስድስት ወራት ካገኘው ገቢ መካከል 50 ነጥብ 4 በመቶው ከድምጽ እንዲሁም 28 ነጥብ 8 በመቶው ከኢንተርኔት አገልገሎት የተገኘ መሆኑን ነው የተናገሩት፡፡


አፈጻጸሙ የእቅዱ 86 ነጥብ 4 በመቶ መሆኑን የገለጹት ዋና ስራ አስፈፃሚዋ በሰሜኑ ጦርነት ምክንያት የኢንተርኔት አገልግሎት መቋረጥና ተንቀሳቅሶ መሥራት ባለመቻሉ እቅዱን ማሳካት አልተቻለም ብለዋል፡፡ በጦርነቱ ሳቢያ የወደሙ ንብረቶችን ለመጠገን በርካታ ወጭ በማስፈለጉና መገኘት የነበረበት ገቢ
ባለመገኘቱ ተቋሙ 4 ቢሊዮን ብር አጥቷል ተብሏል፡፡

ኢትዮ ቴሌኮም አሁን ላይ የደንበኞቹን ቁጥር 60 ነጥብ 8 ሚሊዮን ማድረሱ የተገለጸ ሲሆን ይህም ካለፈው አመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር የ20 በመቶ ብልጫ አሳይቷል ነው የተባለው፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button