Africa

በዙምባበዌ በተከሰተ የመኪና አደጋ በትንሹ 47 ሰዎች ሞተዋል ተባለ

በዙምባበዌ በተከሰተ የመኪና አደጋ በትንሹ 47 ሰዎች ሞተዋል ተባለ

አርትስ 29/02/2011

 ትናንት ምሽት ከሙታሬ ወደ ሃራሬ በመጓዝ ላይ የነበረዉ ቦልት ከተር የተሰኘ አዉቶብስ በተቃራኒ አቅጣጫ ከሚጓዘዉ ስማርት ኤክስፕረስ አዉቶብስ ጋር ተጋጭተዉ በትንሹ የ47 ሰዎች ህይወት ማለፉን ዜድ ቢሲ ዘግቧል፡፡

የሃገሪቱ ትራንስፖርት ሚኒስትር ቢጊ ማቲዛ በበኩላቸዉ ከትራፊክ ፖሊስ የሚላከዉን መረጃ እየጠበቅን ነዉ ለአሁን ግን በአደጋዉ 30 ሰዎች መሞታቸዉን ብቻ ነዉ የሰማነዉ በዚህም ጥልቅ ሃዘን ተሰምቶናል ብለዋል፡፡

አዉቶብሶቹ የተጋጩበት ምክኒያት ባይገለፅም የሟቾቹ ቁጥር ሊጨምር እንደሚችል ኒዉ ዙምባበዌ ዶት ኮም ዘግቧል፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button