EthiopiaPoliticsRegionsSocial

አዲስ አበባ ቦሌ ሩዋንዳ አካባቢ 3 ሚሊዮን 5መቶ ሺህ የኢትዮጵያ ብር እና 61ሺህ 400 የአሜሪካ ዶላር ተያዘ፡፡

አርትስ 11/01/2011
ገንዘቡን ሁለት ቻይናዊያን እና አንድ ኢትዮጲያዊ አመሻሽ ላይ ቦሌ ሩዋንዳ አካባቢ
ወደሌላ መኪና በመጫን ሲያሸሹ ነው በፖሊስ የተያዙት፡፡
በወቅቱም የፖሊስ አባላቱን ሁለት ሚሊዮን ብር ሰጥተዋቸው እንዲለቋቸው ጠይቀው እንደነበር አባላቱ ተናግረዋል፡፡
የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ለአርትስ እንደገለፀው ቻይናዊያኑ ቻይና ስቴት ኮንስትራክሽን ከተሰኘ ተቋም ማታ ማታ በካርቶን የታሸጉ ብሮችን እንደሚያወጡ ፖሊስ ጥቆማ ደርሶት ነው ክትትሉን የጀመረው፡፡
በጥቁር ገበያ በርካታ ቁጥር ያላቸው የገንዘብ ኖቶች እንደሚንቀሳቅስ እና ይህን ለመግታት ህብረተሰቡ ከፖሊስ ጋርበጋራ መቆም እንዳለበት ፖሊስ አሳስቧል፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button