Africa

ኤች አር 6600” እና “ኤስ 3199” ረቂቅ ሕጎችን የሚቃወም ሰልፍ በኒው ጀርሲ ግዛት ተካሄደ::

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 13፣ 2014 ኤች አር 6600” እና “ኤስ 3199” ረቂቅ ሕጎችን የሚቃወም ሰልፍ በኒው ጀርሲ ግዛት ተካሄደ:: በትናትናው ዕለት በ “ኤስ 3199” ረቂቅ ሕግ አርቃቂ ሴናተር ሮበርት ሜኔንዴዝ (ኒው ጀርሲ) ቢሮ ፊት ለፊት በተከናወነው ሰልፍ ላይ “ረቂቅ ሕጎቹ ኢትዮጵያንና ኤርትራን የሚጎዱ ናቸው”፣ ”ማዕቀብ ይገድላል ማዕቀብ ምንም አይጠቅምም”፣ “ኤች አር 6600” እና “ኤስ 3199” ይሰረዙ እና “ሕጎቹ የኢትዮጵያና አሜሪካን ግንኙነት” የሚጎዱ ናቸው” የሚሉ መልዕክቶች ተላልፈዋል።


“ሮበርት ሜኔንዴዝ ሽብርተኞችን መደገፍ ያቁሙ”፣ “ሜኔንዴዝ ያረቀቁት ሕግ ኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያንን የሚጎዳ ነው”፣ “በሴኔት ምርጫው ለሮበርት ሜኔንዴዝ ድምጽ አንሰጥም” እና “የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም በሚጎዳ ተግባር የሚንቀሳቀሱ የአሜሪካ ባለስልጣናትን በምርጫው በድምጽ መቅጣት አለብን” ሲሉ ሰልፈኞቹ መግለጻቸውን ኢዜአ ከኒው ዮርክ ኒው ጀርሲ ተስፋ ለኢትዮጵያ ድርጅት ያገኘው መረጃ ያመለክታል። በኒው ጀርሲ፣ኮኔቲከት፣ፊላደልፊያና ኒው ዮርክ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን፣ኤርትራውያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች በሰልፉ ላይ መሳተፋቸው ተገልጿል።

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button