Africa

በጦርነት በደቀቀችው ሞቃዲሹ የኢንተርኔት ግብይት ተሟሙቋል

ከ25 አመት ላላነሰ ጊዜ በጦርነት የደደቀችውና መንግስት አልባ ሆና የኖረችው  ሶማሊያ ከወደቀችበት ማንሰራራት ጀምራለች። በሞቃዲሾ የኢንተርኔት ገበያ ተሟሙቋል ይላል የሬውተርስ ዘገባ።

እስካሁን የፖስታ አገልግሎት ያልተጀመረባት እና ከአጠቃላይ ህዝቧ ከሁለት በመቶ በታች ብቻ ኢንተርኔት ተጠቃሚ የሆነባት ሶማሊያ ውስጥ የኦንላይን ገበያ መጀመሩ ብዙዎችን አስደንቋል።

የዜና ወኪሉ ያናገራትና ሞቃዲሹ ውስጥ በሚገኝ ጎልደን ዩኒቨርሲቲ በተባለ የትምህርት ተቋም ውስጥ የሂሳብ ሰራተኛ የሆችው ሳፊያ “የኢንተርኔት ገበያ በጣም ይመቸኛል፣እኔ ወደገበያ ለመውጣት ጊዜ የለኝም” ብላለች።

“እኛ ሃገር ያሉት የኢንተርኔት ገበያ መስራቾች አዲስ እንደመሆናቸው ሁሉንም ነገር ፈልገህ ላታገኝ ትችላለህ። ከጊዜ ወደጊዜ ግን እድገት እያሳዩ ነው። የምንፈልገውን ሁሉ በቅርብ ጊዜ እንደሚያቀርቡልን ደግሞ አምናለሁ” ብላለች ሳፊያ ለዜና ወኪሉ።

ሶማር የተባለው እና ከተመሰረተ ሁለት አመት የሞላው የሶማሊያ የኢንተርኔት ገበያ አሁን ባለው አቅሙ ከትኩስ አሳ እስከ ኤሌክትሮኒክስ እና የቢሮ እቃዎች ድረስ የሚያቀርብ  ሲሆን በወር እስከ 25ሺህ የሚደርስ የኢንተርኔት ግዢ ትዕዛዝ ተቀብሎ ዕቃዎቹን በየቤቱ ያደርሳል።

ኩባንያው የታዘዘውን እቃ በየቤቱ የሚያደርሰው በሞተርሳይክል  እና በመኪና ሲሆን መሃመድ የተባለ የኩባንያው የሽያጭ ወኪል “በጦርነት የተጎዳው የከተማዋ መንገድ ፈተና ቢሆንብም ስራችንን ግን እየሰራን ነው” በማለት ተናግሯል

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button