Uncategorized

የቴህራንና የደማስቆ መስማማት እስራኤልን አስቆጥቷል፡፡ 

ሶሪያና ኢራን በደህንነት ዙሪያ በጋራ ለመስራት ባደረጉት አዲስ ስምምነት የተከፉት የእሰራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤናሚን ኔታንያሁ የሁለቱን ሀገራት ስምምነት ተቀባይነት የሌለው ብለውታል፡፡
ጠቅላይ ሚንስትሩ አክለውም የፕሬዝዳንት ሀሰን ሮሀኒ አስተዳደር ከእንዲህ ዓይነቱ ድርጊት የማይቆጠብ ከሆነ ሶሪያ ውስጥ በሚገኘው የኢራን ጦር ላይ የማያዳግም ርምጃ እንደሚወስዱ አስጠንቅቀዋል፡፡
አልጀዚራ እንደዘገበው ኢራን በሶሪያ ያላትን ወታደራዊ እንቅስቃሴ ለመግታት እስራኤል ተግታ እየሰራች ነው፡፡
ኔታናያሁ ያን አስቀያሚ የኒውክሌር ስምምነት ሙሉ ተቀባይነት እንዳይኖረው ያደረግነው ጥረት እንደተሳካልን ሁሉ ቴህራን በሶሪያ ያላትን ወታደራዊ ተሳትፎ ለማስቀረትም ዳተኝነት አናሳይም ብለዋል፡፡
በሶሪያ የሚገኘው የኢራን የዲፕሎማሲ ጸህፈት ቤት በበኩሉ ቴህራን ለደማስቆ የምታደርገው ወታደራዊ ድጋፍ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቋል ፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button