Uncategorized

በርካታ እስራኤላውያ በኔታኒያሁ ውሳኔ ቅር ተሰኝተዋል

አርትስ 07/03/2011
ጠቅላይ ሚኒስትር ቤናሚን ኔታኒያሁ ከጋዛ ጋር ያደረጉትን የተኩስ አቁም ስምምነት አስመልክቶ
የተደረገ የዳሰሰሳ ጥናት እንደሚያሳየው ብዙዎቹ የእስራኤል ዜጎች ደስተኞች አይደሉም፡፡
ሚድል ኢስት ሞኒተር እንደዘገበው በጥናቱ ከተካቱት 500 እስራኤላውያን መካከል 74 በመቶ
የሚሆኑት ቅሬታ እንደገባቸው ተናግረዋል፡፡
እነዚህ ዜጎች ሀገሪቱን በመንግስትነት የሚያስተዳድርው የቤናሚን ኔታኒያሁ ሊኩድ ፓርቲ በእስራኤልና
በጋዛ መካከል ያለውን ቀውስ የመፍታት አቅሙን ይጠራጠራሉ፡፡
ሮይተርስ ይዞት በወጣው ዘገባ ደግሞ ኔታኒያሁ ከምክር ቤት አጋሮቻቸው አስቸኳይ ምርጫ መካሄድ
አለበት የሚል ግፊት በርክቶባቸዋል፡፡
ኔታኒያሁ ከጋዛ ጋር ባደረጉት የተኩስ አቁም ያልተስማሙት የመከላከያ ሚኒስትሩ አቪግዶር ሌበርማን
በቅርቡ ስራቸውን መልቀቃቸው ይታሰወሳል፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button