EthiopiaSocial

ኪዳን ኢትዮጵያ በሃገሪቱ ለዉጥ እንዲመጣ የታገሉ ባለዉለታዎችን ሊሸልም ነዉ፡፡

ላለፉት ሃምሳ አመታት በኢትዮጵያ ለዉጥ እንዲመጣ በርካቶች ሞተዋል፤ ብዙዎች ለእስር ተዳርገዋል ያሉት የኪዳን ኢትዮጵያ ፕሮግራም አዘጋጅ አቶ መስፍን ሰለሞን ለለዉጡ መምጣት ዋጋ የከፈሉ ጀግኖችን አለመዘከር ታሪክን መርሳት ነዉ ብለዋል፡፡
ዛሬ በአገሪቱ ነፃነትና ሰላም መጣ እንጂ መሰረት አልተጣለም፤ የተረጋገጠ ሰላም ለማምጣትና ነፃነትን ለመገንባት የለዉጡ ሃዋሪያ የሆኑ ጀግኖችን ኪዳን ማስገባት ጠቃሚ ነዉ ሲሉ አቶ መስፍን በመግለጫቸዉ አስታዉቀዋል፡፡
በሃገሪቱ ለዉጥ መምጣት ግንባር ቀደም በመሆን ህዝቡን በመምራት ላይ የሚገኙ የመንግስት ባለስልጣናትን ጨምሮ ለዴሞክራሲ ልዕልና ሲታገሉ የነበሩ ፖለቲከኞች አክቲቪስቶች ጦማሪያን የሚዲያና የኪነጥበብ ባለሙያዎች ኪዳን ኢትዮጵያ ለመሸለምና ኪዳን ለመስጠት ከያዛቸዉ ዘርፎች መካከል ተጠቃሽ ሲሆኑ ፤ ምርጫዉም በህዝብ አማካኝነት እንደሚደረግ የኪዳን ኢትዮጵያ አዘጋጆች ለአርትስ ተናግረዋል፡፡

አርትስ 24/12/2010

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button