EthiopiaSocial

ጷግሜ ወርን እንደ አንድ የኢትዮጵያዊነት መገለጫ እና የቱሪስት መሳቢያ መንገድ መጠቀም ይገባል ተባለ

አርትስ 25/12/2010
የጷግሜ ወር አዲስ ዓመትን መቀበያ ጊዜ ከመሆኑ አንፃር ከመደበኛ ስራ ይልቅ እራስን የሚያዘጋጁ እና ከሌሎች ጋር ትውውቅን በሚፈጥሩ መንገዶች ለማሳለፍ እንዲቻል በሂደት ላይ እንደሆነ ተነግሯል፡፡
ይህ የተባለው የጷግሜ ፌስቲቫል አዘጋጆች ፌስቲቫሉን አስመልክቶ ዛሬ በካፒታል ሆቴል በሰጡት መግለጫ ላይ ነው፡፡
ክብረ በዓሉ ከጷግሜ 1ቀን እስከ ጷግሜ 4 ቀን 2010 ዓ.ም በጉለሌ የዕፅዋት ማዕከል ውስጥ እንደሚካሄድ ነው የተገለፀው፡፡
የጷጉሜ ፌስቲቫል ዋና አዘጋጅ አቶ ሃይለአብ መረሳ እንደተናገሩት በሌሎች ሀገራት በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚከበሩ ክብረ በዓላት ይካሄዳሉ እኛም የኢትዮጵያ ልዩ ገፅታ የሆነውን ጷግሜ ወርን ተጠቅመን አዘጋጅተናል ብለዋል፡
በዝግጅቱ የደም ልገሳ፣ከተለያዩ የሃገሪቱ ክፍሎች በሚመጡ ቡድኖች የባህል ልውውጥ፣የፓናል ውይይቶች፣በበጎ አድራጎት ድርጅቶች የሚቀርቡ መሰናዶዎች እና ችግኝ የመትከል መርሃ ግብሮችን ያካተተ እንደሆነ አዘጋጆቹ ገልፀዋል፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button