SportSports

የኮፓ ዴል ሬይ የፍፃሜ ጨዋታ ነገ ምሽት ይደረጋል፡፡

117ኛው የስፔን ኮፓ ዴል ሬይ ወይንም የስፔን ንጉስ ዋንጫ የፍፃሜ ጨዋታ በነገው ዕለት ምሽት 4፡00 ሰዓት ላይ ይደረጋል፡፡

ግጥሚያው በባርሴሎና እና ቫሌንሲያ መካከል ሲቪያ ውስጥ በሚገኘው በሪያል ቤትስ ቤኒቶ ቪያማሪን ስታዲየም ይደረጋል፡፡

በአሰልጣኝ ኤርኔስቶ ቫልቬርዴ የሚመራው የካታላኑ ቡድን በግማሽ ፍፃሜው ተቀናቃኙን ሪያል ማድሪድ በደርሶ መልስ 4 ለ 1 ድል በማድረግ ለተከታታይ ስድስተኛ የፍፃሜ ጨዋታ ሲበቃ የተመሰረተበትን መቶኛ ዓመት እያከበረ የሚገኘው የማርሴሊኖው ቡድን ቫሌንሲያ ደግሞ ሪያል ቤቲስን 3 ለ 2 ማሸነፍ ችሏል፡፡   

ባርሳ 41ኛውን የፍፃሜ ጨዋታ የሚያደርግ ሲሆን ለአምስተኛ ተከታታይ ድሉ፤ በአጠቃላይ ደግሞ ለ31ኛ የንጉስ ዋንጫ ድሉ ይጫወታል፡፡ ቫሌንሲያ እስካሁን 7 ጊዜ ዋንጫውን ከፍ ያደረገ ሲሆን ለስምንተኛ ድሉ ይፋለማል፡፡

ቫሌንሲያ ዋንጫውን ለመጨረሻ ጊዜ ያነሳው በ2008 ቪንሴንቴ ካልዴሮን ላይ ሄታፌን 3 ለ 1 በማሸነፍ ነበር፡፡

ጨዋታው በአርቢትር አልቤርቶ ኡንዲያኖ ማዬንኮ ይመራል፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button