EthiopiaNews

እስከ ሰኔ ወር መጨረሻ 1 ነጥብ 5 ሚሊየን ኩንታል ምርት መሰብሰብ መቻሉን የፌደራል ህብረት ስራ ኤጀንሲ አስታወቀ፡፡

አዲስ አበባ፣ሐምሌ17፣ 2012 እስከ ሰኔ ወር መጨረሻ 1 ነጥብ 5 ሚሊየን ኩንታል ምርት መሰብሰብ መቻሉን የፌደራል ህብረት ስራ ኤጀንሲ አስታወቀ፡፡ኮሮና ቫይረስን ምክንያት በማድረግ ሊፈጠር የሚችል ተገቢነት የሌለው የዋጋ ግሽበትን ለመከላከልና የምርት እጥረት እንዳይከሰት በተሰራ የተቀናጀ ስራ ከክልል አምራች ኅብረት ሥራ ማኅበራት 1 ነጥብ 5 ሚሊየን ኩንታል ምርት መሰብሰብ መቻሉ ተገልጿል፡፡

ከተሰበሰበው ምርት ውስጥ ከ875 ሺህ ኩንታል በላይ ምርት ለሸማቹ ማህበረሰብ በተመጣጣኝ ዋጋ ማቅረብ መቻሉም ነው የተገለፀው፡፡እንዲሁም የግብርና ምርቶች እንዲሰበሰቡና የምርት አቅርቦቱ ሳይቆራረጥ እንዲቀጥል ለማድረግ የፌደራል ኅብረት ሥራ ኤጀንሲ ከክልል የኅብረት ሥራ
aኤጀንሲ አመራሮችና ከኅብረት ሥራ ማህበራት አመራሮች እና ባለሙያዎች ጋር በቅንጅት እየተሠራ መሆኑን ከፌደራል ህብረት ስራ ኤጀንሲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button