EthiopiaNewsPolitics

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይና ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ በኬንያ በተፈጸመው የሽብር ጥቃት ለተጉዱት መፅናናትን ተመኝተዋል

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይና ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ በኬንያ በተፈጸመው የሽብር ጥቃት ለተጉዱት መፅናናትን ተመኝተዋል

ሁለቱ መሪዎች ከትናንት በስቲያ በናይሮቢ በሚገኝ ዘመናዊ ሆቴል በተፈጸመ የአጥፍቶ ጠፊዎች ጥቃትየ15 ሰዎች ህይዎት ማለፍ ላይ የተሰማቸውን ጥልቅ ሀዘን ገልፀዋል፡ ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘወዴ በኬንያ የተፈጸመውን የሽብር ጥቃት በማውገዝ ለኬንያ ህዝብና መንግስት መፅናናትን ተመኝተዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመዲናዋ ናይሮቢ በንጹሃን ዜጎች ላይ የተፈጸመውን ጥቃት በመንግስታቸው ስም አውግዘዋል። ለተጎጅ ቤተሰቦችና ለመላው ኬንያውያንም መፅናናትን እንደተመኙ ከጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት የተገኘው መረጃ ያመላክታል።

በተመሳሳይ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ለኬንያ ህዝብና መንስግስት መፅናናትን የተመኙ ሲሆን ኢትዮጵያ ሽብርተኝነትን ለመዋጋት ከኬንያ ጎን እንደምትሆን አስታውቀዋል፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁም በኬንያ የተፈፀመውን የሽብር ጥቃት በፅኑ ማውገዛቸው ይታወሳል፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button