Ethiopia

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በአማራ እና አፋር ክልሎች የደረሱ ሰብዓዊና ቁሳዊ ውድመቶችን ላጠና ነው አለ፡፡

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 25፣ 2014 የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር ጣሰው ወልደ ሃና ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንዳሉት ጦርነት በነበረባቸው የአማራና አፋር ክልሎችና በአንዳንድ አካባቢዎች የደረሰውን የሕይወትና የንብረት ውድመት በመስክ የሚያጠና ግብረ-ኃይል ተቋቁሞ የጥናትና የምርምር ስራውን ጀምሯል። ከጥናትና ምርምር ቡድኑ የሚደርስበት ግኝት ውድመቱን ያደረሰውን አሸባሪ ቡድን የታሪክ ተወቃሽ በማድረግ በቀጣይ ለሚኖሩ የጥናትና ምርምር ስራዎች ይውላል ብለዋል።


አሸባሪ ቡድኑ የፈጸማቸውን ሰብዓዊና ቁሳዊ ውድመቶች በተደራጀ መልኩ በማጥናት መጪው ትውልድ የሽብር ቡድኑን አረመኔነት እንዲገነዘብና ኢትዮጵያም ያለፈችበትን የታሪክ ውጣ ውረድ ሰንዶ ለማስቀመጥ ይረዳል ብለዋል። ከጥናትና ምርምሩ ጎን ለጎንም በአሸባሪ ቡድኑ የወደሙ ዩኒቨርሲቲዎችን መልሶ ለማቋቋምም
ዩኒቨርሲቲው ግብረ ኃይል አቋቁሞ ተግባራዊ እንቅስቃሴ መጀመሩንም ፕሬዚዳንቱ ተናግረዋል፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button