Uncategorized

በኢንዶዥያ በጎርፍ አደጋ  የሟቾች ቁጥር ሲጨምር  በሺህ የሚቆጠሩት ተፈናቅለዋል

በኢንዶዥያ በጎርፍ አደጋ  የሟቾች ቁጥር ሲጨምር  በሺህ የሚቆጠሩት ተፈናቅለዋል ፡፡

በሀገሪቱ የጣለው ከባድ ዝናብ ባስከተለው የጎርፍ እና የመሬት መንሸራተት አደጋ 59 ሰዎች ህይዎታቸው ማለፉን የሀገሪቱ ባለ ስልጣናት  አረጋግጠዋል፡፡

አልጀዚራ እንደዘገበው አደጋው በተከሰተባቸው አካባቢዎች መንገዶች መዘጋታቸው ለተጎጂዎቹ አስፈላጊውን እርዳታ ለማድረግ እንቅፋት ፈጥሯል፡፡

ባለ ስልጣናቱ እና የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች እንዳሉት አከሞቱት  ሰዎች በተጨማሪ 24 ሰዎች የገቡበት አይታወቅም፡፡

አደጋው ትምህርት ቤቶች፣ የመንግስት ተቋማት እና ድልድዮች ላይ ከፍተኛ ጉዳት አድርሷል፤ 3 ሺህ 400 ነዋሪዎች ደግሞ አካባቢያቸውን ለቀው እንዲወጡ ተገደዋል፡፡

የመቁሰል አደጋ የደረሰባቸው ሰዎች በየሆስፒታሉ እርዳታ እተደረገላቸው ሲሆን  ከቤት ንብረታቸው የተፈናቀሉት በሀይማኖት ተቋማት ተጠልለው ይገኛሉ ፡፡

ከጥቅምት እስከ ሚያዚያ ባሉት ወራት በአብዛኛው ደቡባዊ እስያ  ዝናብ ስለሚበረታ በኢንዶኔዥያ  የጎርፍ እና መሬት መንሸራተት አደጋ የተለመደ ነው፡፡

የሀገሪቱ የሚትዎሮጂ ተቋም እና የአካባቢው ባለ ስልጣናት ነዋሪዎች ይህን ተረድተው አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርጉ አሳስበዋል፡፡

 

 

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button