EthiopiaPoliticsRegionsSocial

ወቅቱ ምክንያቶችን ፈልገን የምንጣላበት ሳይሆን ምክኒያት ፈጥረን አንድነታችንን የምናጠናክርበት መሆን ኣለበት ተባለ

አርትስ 04/01/2011
የኦሮሚያ ክልል መንግስት ኮሚኒኬሽን ፅ/ቤት ሃላፊ ዶ/ር ነገሪ ሌንጮ ዛሬ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ነው ይህን ያሉት፡፡
ሃላፊው አክለውም ወቅቱ ምክንያቶችን ፈልገን የምንጣላበት ሳይሆን ምክኒያት ፈጥረን አንድነታችንን የምናጠናክርበት መሆን ኣለበት ብለዋል፡፡
የትኛውም አካል ይወክለኛል ያለውን ሰንደቅ ዓላማም ሆነ አርማ መያዝ ይችላል ያሉት ዶ/ር ነገሪ ፤የተከፈለው መስዋትነትም ይህን አይነት እኩልነትና ነፃነት ለማምጣት ነው ብለዋል፡፡ ስለሆነም ወጣቱ እየተደረጉ ያሉ ህገወጥ እንቅስቃሴዎችን በትዕግስት ማለፍ አለበት ሲሉ አሳስበዋል፡፡
በአዲስ አበባ በአንዳንድ ስፍራዎች በትናንትናውና በዛሬው ዕለት ሰንደቅ ዓላማ እንዳይሰቀል እየተደረገ ያለው እንቅስቃሴ በየትኛውም መመዘኛ ተቀባይነት የለውም ብለዋል ዶ/ር ነገሪ በመግለጫቸው፡፡
በመሆኑም በሰንደቅ ኣላማ ምክኒያት ምንም ዓይነት ችግር እንዳይፈጠር አሳስበው፤ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮችን ለመቀበል እየተደረገ ባለው ሥነ ሥርዓት ላይ የሚታዩ ማንኛውንም ጎጂ እንቅስቃሴዎች ለፀጥታ አካላት በመጠቆም ትብብር እንዲያደርጉ ለማህበረሰቡ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button