EthiopiaPoliticsSocial

በተለያዩ ምክንያቶች የከዱ ፌዴራል ፓሊስ አባላት በምህረት አዋጁ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ጥሪ ቀረበ::

ከሰራዊቱ በተለያዩ ምክንያት የከዱ (የኮበለሉ) አባላት እና የፖሊስ አመራሮች መንግስት ባስቀመጠው የምህረት አዋጅ ተጠቃሚ እንዲሆኑ የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ጥሪ አቀረበ።
ኮሚሽኑ መንግስት ባስቀመጠው የምህረት አዋጅ መሰረት እስከ ግንቦት 30/2010
ዓመተ ምህረት ድረስ ከሰራዊቱ የከዱ አባላትና አመራሮች ተጠቃሚ ይሆናሉ።
የኮበለሉት የፌዴራል ፖሊስ ሰራዊት አባላት ከነሀሴ መጨረሻ ጀምሮ በመጪዎቹ ስድስት ወራት በምህረት አዋጁ መሰረት ተጠቃሚ እንደሚሆኑ በኮሚሽኑ የህግ ጉዳይ ምክር አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ኮማንደር ፋሲል አሻግሬ ተናግረዋል።
በአዲስ አበባና በዙሪያዋ የሚገኙ በከተማ ፖሊስ ኮሚሽን፣ በፌደራል ፖሊስ ዋናው መስሪያ ቤት እንዲሁም በወንጀል መከላከል ዘርፍ ዳይሬክቶሬቶች በመገኘት ሪፖርት ማድረግ የሚችሉ ሲሆን፥ በክልል የሚገኙት ደግሞ ለክልላቸው ፍትህ ቢሮ ሪፖርት በማድረግ በምህረቱ ተጠቃሚ መሆን እንደሚችሉ ታውቋል።
ከዚህ በተጨማሪ በዲሲፒሊን ምክንያት ከሰራዊቱ የተቀነሱ አባላት እና አመራሮች ከዚህ ቀደም የወሰዱትን ደብዳቤ ተመላሽ በማድረግ በምትኩ ሌላ የስንብት ደብዳቤና የስራ ልምድ ማግኘት እንደሚችሉ ታውቋል።
የምህረቱ ተጠቃሚ የሆኑ አባላት የወሰዱትን የመንግስት ንብረት ሪፖርት ለሚያደርጉበት ተቋም በመመለስ የነጻነት የምስክር ወረቀት መውሰድ እንደሚጠበቅባቸው ተነግሯል።
ሆኖም በዲሲፒሊን ምክንያት ከሰራዊቱ የተቀነሱ ፖሊሶች ወደ ስራ ቦታ እንደማይመለሱ የስራ አመራሩ ውሳኔ እንዳሳለፈ ኮማንደር ፋሲል አሻግሬ አስታውቀዋል።
ኤፍ.ቢ.ሲ

አርትስ 25/12/2010

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button