EthiopiaPoliticsRegions

በኦህዴድ ዘጠነኛ ድርጅታዊ ጉባዔ መክፈቻ የድርጅቱ ሊቀመንበር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ይገኛሉ ተባለ

አርትስ 06/01/2011

“የላቀ ሀሳብ ለበለጠ ድል” በሚል መሪ ቃል ከመስከረም 8 እስከ 10/2011 ዓ/ም በጅማ ከተማ ይካሄዳል። በጉባዔው የፓርቲዉ ያለፉት ሶስት ዓመታት የድርጅት እና የፖለቲካ ስራዎች የዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት፣ የኦዲት እና ቁጥጥር ኮሚሽን ሪፖርት፣ የፓርቲዉ ቀጣይ ስትራቴጂክ አቅጣጫዎች ቀርበዉ ዉይይት ተደርጎባችዉ እንድሚፀድቁ ይጠበቃል።
ፓርቲዉ በዚህ ጉባዔ በአዲስ ስያሜ፣አርማ እና መዝሙር ራሱን ሪብራንድ ያደርጋል። 
በጉባዔዉ የመክፈቻ ስነስርዓት የድርጅቱ ሊቀመንበር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዓብይ አህመድ እንደሚገኙ ታውቋል። ከ6 ሺህ በላይ ተሳታፊዎች በተገኙበት በደማቅ ስነ ስርአት ይከፈታል። በጉባዔዉ ላይ 1070 ተሳታፊዎች በድምፅ 275 ሰዎች ደግሞ በታዛቢነት ይሳተፋሉ።
በጉባኤዉ በርካታ አዳዲስ ወጣት ምሁራን በማዕከላዊ ኮሚቴ አመራርነት ይመረጣሉ ተብሎ ይጠበቃል።

የኦህዴድ የገጠር ፖለቲካ አደረጃጀት ዘርፍ ሃላፊና የ9ኛው ጉባዔ ቃል አቀባይ አቶ አዲሱ አረጋ ናቸው መግለጫውን የሰጡት።

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button