EconomyEthiopiaPoliticsSocial

የታላቁ ኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ሰራተኞች የስራ ማቆም አድማ መቱ::

የታላቁ ኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ሰራተኞች በደመወዝ ጭማሪ ጥያቄና የአገልግሎት አሰጣጥ መሻሻልን በመጠየቅ ላለፉት ሶስት ቀናት የስራ ማቆም አድማ ማድረጋቸውን አስታውቀዋል፡፡
ሰራተኞቹ ለኢቢሲ እንደገለፁት በግድቡ ግንባታ ላይ አሻራቸውን እያሳረፉ ቢሆንም የሚከፈላቸው ክፍያ አናሳ መሆኑ ኑሯቸውን ከባድ እንዳደረገባቸው ተናግረዋል፡፡
ከዚህ በተጨማሪ በግንባታው ተቋራጭ በኩል ከደመወዝ ክፍያ ማነስ በተጨማሪ፣ የሰራተኛ አያያዝ ችግር፣የሰራተኞች ምግብ ቤት የጥራት ችግርና የዋጋ መናር የስራ ማቆም አድማ እንዲያደርጉ እንዳስገደዳቸው ተናግረዋል፡፡
የታላቁ ኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ኤፍሬም ወ/ኪዳን ሰራተኞቹ ላለፉት ሶስት ቀናት የስራ ማቆም አድማ ላይ መሆናቸውን አረጋግጠዋል፡፡
ሰራተኞቹ ያቀረቡትን ችግር ለመፍታት ውይይቶች በመደረግ ላይ መሆናቸውንም ገልፀዋል፡፡

አርትስ 23/10/2010

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button