SportSports

በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ማድሪድ፤ ማንችስተር ዩናትድ፤ ባየር ሙኒክ እና ዩቬንቱስ ድል ቀንቷቸዋል

አርትስ ስፖርት 10/1/2011
ከምድብ አምስት እስከ ስምንት የሚገኙ ክለቦች ትናንት ምሽት የሻምፒዮንስ ሊግ የምድብ የመጀመሪያ ጨዋታዎቻቸውን አካሂደዋል፡፡
ምድብ አምስት ላይ ባየር ሙኒክ በሉዋንዶውስኪ እና ሳንቼዝ ግቦች ቤኔፊካን 2 ለ 0 ሲረታ አያክስ ኤ.ኢ.ኬ አቴንስን 3 ለ 0 መርታት ችሏል፡፡
በስድስተኛው ምድብ ማንችስተር ሲቲ በሜዳው በሊዮን የ2 ለ1 ሽንፈት አስተናግዷል፤ እዚሁ ምድብ ላይ ሻክታር ዶኔስክ ከ ሆፈንየም በሁለት አቻ ውጤት ተለያይተዋል፡፡
ሪያል ማድሪድ በሜዳው ሳንቲያጎ ቤርናቦ ሮማን 3 ለ 0 ሲያሸንፍ፤ ኢስኮ፣ ቤል እና ማርያኖ ግቦችን መረብ ላይ አሳርፈዋል፤ ክለቡም ያለ ክርስትያኖ ሮናልዶ የሻምፒዮንስ ሊግ ጉዞውን በድል ጀምሯል፡፡ በምድብ ሰባት ሌላ ጨዋታ ቪክቶሪያ ፕለዘን ከ ሲ.ኤስ.ኬ.ኤ ሞስኮው 2 ለ 2 አቻ ተለያይተዋል፡፡
በመጨረሻው ምድብ ስምንት ወደ ሲውዘርላንድ ያቀናው ማንችስተር ዩናይትድ ያንግ ቦይስን 3 ለ 0 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል፡፡ ፖል ፖግባ ሁለት ግቦችን ሲያስቆጥር፤ ማርሽያል ቀሪዋን የማሸነፊያ ጎል ከመረብ አገናኝቷል፡፡
ሜስቲያ ላይ ቫሌንሲያ በዩቬንቱስ የ2 ለ 0 ሽንፈት አስተናግዷል፡፡ ሚራለም ፒያኒች በፍፁም ቅጣት ምት ሁለቱንም ግቦች አስቆጥረዋል፡፡ እዚህ ጨዋታ ላይ ክርስትያኖ ሮናልዶ የቫሌንሲያውን ተከላካይ ጄሰን ሙሪሎ ፀጉር ይዘሀል በሚል የዕለቱ ዳኛ ፍሊክስ ብሪች ከጎል ጀርባ ከሚገኙት አጋዥ ዳኛ ጋር በመነጋገር በ29ኛው ደቂቃ በቀይ ከሜዳ አሰናብተውታል፡፡ ይህን ተከትሎ ሮናልዶ እስከ ሶስት ጨዋታዎች ድረስ ቅጣት ሊጠብቀው እንደሚችል ተነግሯል፡፡
የሻምፒዮንስ ሊግ የምድብ ሁለተኛ ጨዋታዎች ከ12 ቀናት በኋላ ጥቅምት 22 እና 23/2011 ዓ/ም ይካሄዳሉ ተብሏል፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button