SportSports

አርሰናል፤ ቼልሲ፤ ኤስ ሚላን እና ሲቪያ በኢሮፓ ሊግ ድል ቀንቷቸዋል

አርትስ ስፖርት11/01/2011
ትናንት ምሽት የ2018/19 የኢሮፓ ሊግ የምድብ መጀመሪያ 24 ጨዋታዎች በተለያዩ የአውሮፓ ከተማ ስታዲየሞች ተካሂደዋል፡፡
ወደ ግሪክ ያቀናው ቼልሲ ተሰሎንቄ ላይ ፓኦክ ሳሎኒካን በዊሊያን ብቸኛ ግብ 1 ለ 0 አሸንፎ ተመልሷል፡፡ ሰማያዊዎቹ ሰፊ የጨዋታ ብልጫ ቢኖራቸውም ተጨማሪ ግቦችን ግን ማስቆጠር አልቻሉም፡፡
አርሰናል በሜዳው የዩክሬኑን ቮርስክላ ፖልታቫን 4 ለ 2 ሲረታ፤ የድል ግቦችን ኦባመያንግ (2) ፣ ዊልቤክ እና ኦዚል አስቆጥረዋል፡፡ ለዩክሬኑ ቡድን ቼስናኮቭ እና ሻርፓር ከመረብ አገናኝተዋል፡፡ በመድረኩ ጥሩ ስም ያላቸው ኡናይ ኢምሪ ጉዟቸውን በድል ጀምረዋል፡፡
በምሽቱ ከተደረጉ ሌሎች ጨዋታዎች መካከል በስቴቨን ጄራርድ የሚሰለጥነው ሬንጄርስ ከ ቪያርያል ጋር 2 ለ 2 አቻ ሲለያይ፤ የጋቱሶው ቡድን ኤስ ሚላን ዱደላንጌን በሂጓይን ግብ 1 ለ 0 ረትቷል፡፡ ሲቪያ ደግሞ ስታንዳርድ ሊጅን 5 ለ 1 በሆነ ሰፊ ውጤት ሲያሸንፍ፤ ኢንትራክት ፍራንክፈርት ማርሴን 2 ለ 1፤ ዳይናሞ ዛግሪብ ፌነርባቼን 4 ለ 1፤ ሴልቲክ ሮዘንበረግን 1 ለ 0 በሆነ ውጤት መርታት ችለዋል፡፡
በቀጣይ የምድብ ሁለተኛ ጨዋታዎች በመጭው መስከረም 24/2011 ዓ/ም ይከናወናሉ፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button