SportSports

ኔይማር የብረዚል አምበልነቱን በአልቬስ ተቀምቷል::

የ27 ዓመቱ ብራዚላዊ ኮከብ ኔይማር ዳ ሲልቫ ከስምንት ወራት በፊት የተረከበውን የብራዚል ብሔራዊ ቡድን የአምበልነት ሚና ተነጥቆ ለቅርብ ጓደኛው ዳኒ አልቬስ መስጠቱ ታውቋል፡፡

የብሔራዊ ቡድኑ አሰልጣኝ ቲቴ ይሄንን ውሳኔ ያሳለፉት ተጫዋቹ እያሳየ ባለው ስነ ምግባር ጉድለቶች እንደሆነ ተጠቁሟል፡፡

ኔይማር ከቡድን አጋሮቹ ጋር ስምምነት እንደሌለውም ይነገራል፡፡

በዚህም የፓሪስ ሴንት ዤርማ የቡድን አጋሩ አልቬስ ብራዚል ከኳታር እና ሆንዱራስ ጋር ላለባት የወዳጅነት ጨዋታዎች መሪነቱን ይጀመራል ተብሏል፡፡

የ36 ዓመቱ ተጫዋች ከዚህ ቀደም ብሔራዊ ቡድኑን አራት ጊዜ ያህል በአምበልነት መምራቱ ይታወሳል፡፡   

ከሁለት ሳምንት በኋላ በብራዚል አስተናጋጅነት በሚካሄደው የኮፓ አሜሪካ ዋንጫም ቡድኑን ይመራል ተብሏል፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button