Africa

ካይሮ የሙስሊም ወንድማማቾችን መሪ በእድሜ ልክ እስራት ቀጣች

አርትስ 14/01/2011
የ75 ዓመቱ አዛውንት ሞሀመድ ባዲ በፈንጆቹ 2013 በህግ ከታገደ ቡድን ጋር በመንቀሳቀስ የግድያ ወንጀል ላይ እጃቸው አለበት ተብለው ከ5 ዓመት በፊት ነበር ክስ የተመሰረተባቸው፡፡
ፕረስ ቲቪ እንደዘገበው ባዲ እሳቸው የሚመሩት የሙስሊም ወንድማማቾች ቡድን በደቡባዊ ግብጽ በአንድ ፖሊስ ጠቢያ ላይ ለፈጸመው ጥቃት እና ለተገደሉ ፖሊሶች ዋነኛው አነሳሽ ተደርገው ይቆጠራሉ፡፡
በዚህም ምክንያት ከሌሎች 65 የድርጅቱ አባላት ጋር ጥፋኛ ሆነው በመገኘታቸው የግብጽ ፍርድ ቤት በእድሜ ልክ እስራት እንዲቀጡ ወስኖባቸዋል፡፡
ባለፈው ወር የባዲን ክስ ከሌሎች ተከሳሾች ጋር በተናጠል ያየው የጂዛ ፍርድ ቤት በተመሳሳይ የእድሜ ልክ እስራት እንደፈረደባቸው ይታወሳል፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button