EthiopiaRegionsSocial

በጎንደር የእስልምና እምነት ተከታይ በጎ ፈቃደኞች የመስቀል በዓል የሚከበርባቸውን አካባቢዎች እያጸዱ ነው

አርትስ/15/01/2011
የእስልምና እምነት ተከታዮቹ የመስቀል በዓል ዕለት ደመራ የሚለኮስበትንና የክርስትና ሃይማኖት ተከታዮች የሚያከብሩበትን የጎንደር መስቀል አደባባይ በዛሬው ዕለት እያጸዱ ነው፡፡
የጽዳት ዘመቻቸውን ንጋት 12፡00 የጀመሩ ሲሆን በመስቀል አደባባይ አካባቢ የነበሩ ቆሻሻዎችን አጽድተዋል፤ የግንባታ ቁሳቁሶችንም አንስተዋል፡፡
በጎንደር ከተማ አስተዳደር የሚገኙ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ክርስትና ሃይማኖት ተከታዮች ከዚህ ቀደም የኢድ-አልአድሃ አረፋ በዓል ከመከበሩ አስቀድሞ በዓሉ የሚከበርበትን አካባቢ አጽድተዋል፡፡
በጎንደር ከተማ የሚገኙ የእስልምና ሃይማኖት ተከታዮች ከዚህ በፊትም በጅግጅጋ ከተማ ቃጠሎ የደረሰባቸውን አብያተ ክርስቲያናት ለመጠገን የሚውል የ60 ሺህ ብር ድጋፍ ማድረጋቸው ይታወሳል፡፡
የእስልምና እምነት ተከታዮቹ የመስቀል አደባባይን ሲያጸዱ ‹‹አማኝ የሌላውን እምነት ያከብራል›› በሚል መልዕክት ነው፡፡ ‹‹መቻቻልና መከባበር የቆየ ሃይማኖታዊ ሥርዓታችን ለማስቀጠል ብቸኛ መሣሪያችን ነው›› ሲሉም አስተያየታቸውን ለአማራ ብዙኃን መገናኛ ድርጅት ገልጸዋል፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button