EthiopiaPoliticsRegionsSocial

70 የሚሆኑ የኦሮሚያ ወጣቶች (ቄሮዎች) ጋሞጎፋ ዞን አርባምንጭ ከተማ ድረስ በመሄድ የመስቀል በዓልን ሊያከብሩ ነዉ

አርትስ 15/01/2011

“የምስጋናና የአንድነት ጉዞ” በሚል ወደ አርባ ምንጭ የሚደረገዉ ጉዞ መነሻዉን ቡራዩ አድርጎ 70 የሚሆኑ ወጣቶችን ያሳትፋል፡፡
የኦሮሚያ ክልል መንግስት ኮሙኑዮኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ምክትል ሀላፊ ወ/ሮ ኡሚ አባጀማል ለአርትስ እንደገለጹት የወጣቶቹ የጉዞ ዓላማ የጋሞ አባቶችና የአገር ሽማግሌዎች ላሳዩት ልባዊ ፍቅርና ጥልቅ ለሆነው ወንድማማችነታችን ለማመስገን እና የኦሮሞና የጋሞ ህዝቦች የቆየ ታርካዊ አንድነትና ማህበራዊ መስተጋብር ይበልጥ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ለማድረግ ነዉ ብለዋል፡፡
በአዲስ አበባም ሆነ በቡራዩ ከተማ የተከሰቱ ጥፋቶች የሁለቱንም ማህበረሰብ ወጣቶችን በፍፁም እንደማይወክል ለማስገንዘብና በማያውቁት በተጠመደው የፖለቲካ ወጥመድ ሰለባ የሆኑት ንጹኀን የማህበረሰብ ክፍሎችን ለማፅናናት እንደሆነም ተነግሯል፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button