EthiopiaPoliticsRegionsSocial

10ኛው የደኤህዴን ድርጅታዊ ጉባዔ የተጀመሩ ለውጦችን የሚያስቀጥሉ ውሳኔዎችን ያሳልፋል- አቶ ሚሊዮን ማቲዎስ

 

አርትስ 18/01/2011
10ኛው የደኤህዴን ድርጅታዊ ጉባዔ የተጀመሩ ለውጦችን የሚያስቀጥሉ ውሳኔዎችን እንደሚያሳልፍ የደኢህዴን ምክተል ሊቀመንበር አቶ ሚሊዮን ማቲዎስ ገለፁ።

የደኢህዴን ምክተል ሊቀመንበር አቶ ሚሊዮን ማቲዎስ በ10ኛው ድርጅታዊ ጉበባዔ ላይ ባደረጉት ንግግር፥ ደኢህዴን ባለፉት 27 ዓመታት የክልሉን ብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች ተጠቃሚ የሚያደርጉ ስራዎችን መስራቱን አውስተዋል።

ሆኖም ግን ከኪራይ ሰብሳቢነት፣ አካባቢያዊነት፣ ጎጠኝነት፣ አንዱ አንዱን በጥርጣሬ ከመመልከት እና መሰል ችግሮች ጋር በተያያዘ ፈተናዎች አጋጥሞት እንደነበረም አነስተዋል።

ድርጅቱ ባለፉት ዓመታት ችግሩን ለመፍታት የሚያስችሉ በርካታ ውጤታማ ስራዎቸን በሚያከናውነም አሁነም ቀሪ ስራዎች ይጠብቁታል ብለዋል።

አሁን በየአካባቢው የሚያጋጥሙ ችግሮች ሰላምን የሚያናጉ በመሆኑ ዘላቂ መፍትሄ ያሉት አቶ ሚሊዮን፥ በአሁኑ ወቅት በሀገሪቱ እየመጣ ያለውን ለውጥ ለመቀልበስ እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን ልንከላከል ይገባልም ብለዋል።

በሀገሪቱ እየታየ ያለው ለውጥ ዋነኛ ባለቤቱ ህዝቡ ነው ያሉት አቶ ሚሊየን፥ የዴሞክራሲ ምህዳሩን በማስፋትና የህዝቡን ፍትሃዊ ተጠቃሚነት ማረጋገጥ እንዲቻል የህግ የበላይነትን በማረጋገጥ ለውጡ ግቡን እንዲመታ ማድረግ ያስፈልጋል ሲሉም ተናግረዋል።

10ኛው ድርጅታዊ ጉባዐዔ የህዘቡ መሰረታዊ ጥያቄ በግልፅ ውይይት የሚካሄደድበት፣ ድርጅቱ እራሱን የሚያሻሽልበት እና የለውጥ ጉዞን የሚያፋጥኑ ውሳኔዎች የሚተላለፉበት እንደሚሆንም ጠቁመዋል።

ድርጅቱ በሀገር አቀፍና በክልል ደረጃ የሁለተኛው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅዱ ስኬተማ እንዲሆን የበኩሉን ድርሻ እንደሚወጣ አስታውቀዋል።

በእቅዱ አፈፃፀም ጥንካሬውንና ድክመቱን በመገምገም የሚመለከታቸውን ባለድርሻ አካላት በማሳተፍ ወደ ተግባራዊ እንቅስቃሴ እንደሚገባ ተናግረዋል።

በጉባዔው ለቀጣይ ሁለት ዓመት ተኩል የማዕከላዊ ኮሚቴና የቁጥጥር ኮሚሽን ሆነው የሚያገለግሉ አመራሮች የሚመረጡበት መሆኑንም ገልፀዋል።
ኤፍ.ቢ.ሲ

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button