EthiopiaPoliticsRegionsSocial

ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ማህፀነ ለምለም ጊደር ተበረከተላቸው

አርትስ 25/01/2011

የሃዋሳ ከተማ የንግዱ ማህበረሰብ በትናንትናው ምሽት በሃዋሳ ከተማ ለሚገኙና በኢህአዴግ 11ኛው ጉባኤ ላይ ለታደሙ ጉባኤተኞች እና ከአገር ውስጥም ሆነ ከውጭ አገር ለመጡ እንግዶች የእራት ግብዣ አድርገዋል::

በእራት ግብዣው ላይ የሲዳማ የአገር ሽማግሌዎች እና የሃይማኖት አባቶች ለጉባኤው ስኬት ምርቃትና ጸሎት ያደረጉ ሲሆን: የሃዋሳ ከተማ የንግዱ ማህበረሰብም ለክቡር ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር አብይ አህመድ የውጭ ዝርያ ያላት ከ40-60 ሊትር መታለብ የምትችል የ7ወራት ጊደር በስጦታ አበርክተዋል::

ክቡር ጠቅላይ ሚንስትሩም ምስጋና በማቅርብ ንግግራችውን የጀመሩ ሲሆን ፤በንግግራቸውም ዶሮ ብዙ ጮሃ (አሽካክታ) አንድ ዕንቁላል ጠብ ስታደርግ: ላም ግን ድምጽ ሳታሰማ ብዙ ወተት ትሰጣለች:: ኢህአዴግም እንዲሁ ብዙ ሳያወራ ብዙ ልማት ወደማምጣት የሚሽጋገርበት ጉባኤ እንደሚሆና በስኬትም እንደሚጠናቀቅ ያላቸውን እምነት መግለፃቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ልዩ ሀላፊ አቶ ፍፁም አረጋ አስታውቀዋል።

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button