EducationEthiopiaRegionsSocial

የዩኒቨርሲቲ ምደባ ይፋ ሆነ

አርትስ 25/01/2011
የሃገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ እንዳስታወቀው ዩኒቨርሲቲው ምደባው የተማሪዎችን ውጤት፣ የፊልድ እና የዩንቨርስቲ ምርጫ፣ የዩንቨርስቲዎችን የቅበላ አቅም፣ የወንዶችና የሴቶችን ምጥጥን ማዕከል ባደረገ እንዲሁም የልዩ ድጋፍ ተጠቃሚዎችን /በማጥባት ላይ የሚገኙ ሴቶችን ያገናዘበ መሆኑን ተገልጿል።
እንዲሁም ዓይነ ስውራንን፣ መስማት የተሳናቸውን፣ አካል ጉዳተኞችን/ በተጨማሪም የጤና እክል ያለባቸው እና ከታወቀ የመንግስት ሆስፒታል የሜዲካል ቦርድ ማረጋገጫ ያቀረቡት ላይ የማጣራት ስራዎችን ካካሄደ በኋላ ምደባው መዘጋጀቱን አስታውቋል።፡፡
ተማሪዎች ምደባቸውን በኤጀንሲው ድረ-ገጽ app.neaea.gov.et በመግባት ማየት እንደሚችሉ ነው ኤጀንሲው ያስታወቀው፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button