EthiopiaSocial

የካቲላ (አማራንተስ) ሰብል በኢትዮጵያ በዳቦ በቂጣና በእንጀራ መልክ ለምግብነት እየዋለ ነዉ፡፡

የካቲላ (አማራንተስ) ሰብል በኢትዮጵያ በዳቦ በቂጣና በእንጀራ መልክ ለምግብነት እየዋለ ነዉ፡፡

ሰብሉንም በሁሉም የሀገራችን አካባቢዎች ለማስተዋወቅና በዘመናዊ መንገድ ለማልማት እየተሰራ መሆኑን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ገልጿል፡፡
ሀገር በቀል እዉቀቶችን በአግባቡ በማዘጋጀትና በመጠቀም እሴት ጨምሮ ለህብረተሰቡ አገልግሎት እንዲሰጥና ምረታማነቱ እንዲጨምር ለማድረግ ለሚሰሩ ስራዎች የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ድጋፍ እንደሚያደርግ የሚኒስቴሩ ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ሹመቴ ግዛዉ ተናግረዋል፡፡
የካቲላ (አማራንተስ) ሰብልን በሁሉም የሀገራችን አካባቢዎች ለማስተዋወቅና በዘመናዊ መንገድ ለማልማት እየተሰራ ሲሆን ሰብሉን በማስመልከት አዉደጥናት አካሄዷል፡፡

አማራንተስ በስነ-ምግብ ይዘቱም ሆነ ለጤና ባለው ጠቀሜታ ከዋነኞቹ ሰብሎች በቀዳሚነት የሚመደብ፣ ቅጠሉ ወይም ፍሬው ለምግብነት የሚውል፣ በአለማቀፍ ደረጃ በርካታ ዝርያዎች ያሉት፣ ድርቅን የመቋቋም አቅም ያለውና በተለያየ የአየር ሁኔታ ውስጥ መብቀል የሚችል በመሆኑ በሀገራችን አዘውትረን ከምንጠቀማቸው ሰብሎች በእኩል ደረጃ ልንገለገልበት የምንችል እንደሆነም በጥናት ተረጋግጧል፡፡

ካቲላ ”አማረንተስ” በዓለማችን የተለያዩ ሀገራት ከምግብነት በተጨማሪም ለኮስሞቲክስና ለመድሃኒት መስሪያ ጥቅም ላይ የሚውል ሲሆን በሀገራችን አንዳንድ አካባቢዎችም ለምግብነት እና ለመዳህትት ያገለግላል፡፡
ካቲላ (አማራንተስ) በኢትዮጵያም በዳቦ በቂጣና በእንጀራ መልክ መዘጋጀትና ለምግብነት መዋል ጀምሯል፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button