EconomyEthiopia

ኮርፖሬሽኑ የሀይል ማመንጫ ተርባይኖችን ውል ለጀርመን ኩባንያ በጨረታ ሰጠ።

የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ሊሰራቸው የነበሩ ሶስት የሀይል ማመንጫ ተርባይኖችን ውል ለጀርመን ኩባንያ በጨረታ ሰጠ።

የዛሬ ሁለት ሳምንት የጨረታው ሰነድ ሲከፈት ከእያንዳንዱ ተርባይን የ5 ነጥብ 9 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ቅናሽ መገኘቱን የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን የኮመርሻልና ሲቪል ምርቶች ኦፕሬሽን ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ አብዱልአዚዝ መሀመድ ተናግረዋል።

ጨረታውን የጀርመኑ ቮይስ ኩባንያ ማሸነፉንም ገልጸዋል።

ይህ ኩባንያ ከዚህ ቀደም ከሀይል ማመንጫ ተርባይኖች ውስጥ ስምንቱን ያቀረበ ሲሆን አሁን ደግሞ ሶስቱ ተጨምረውለታል፤ የፈረንሳዩ አሊስቶን ደግሞ አምስቱን የማቅረብ ውል ወስዷል።

በዚህም መሰረት ሜቴክ ከተርባይን ስራዎች ሙሉ ሙሉ ወጥቷል፤ ከዚህ ቀደም በተደረሰው ስምምነት መሰረትም ተርባይኖችን ተክሎ ኮሚሽን የማድረጉ ስራም የአምራቾች እንዲሆን መወሰኑ ይታወሳል።

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button