EthiopiaPoliticsRegionsSocial

በኮዬ ፈጨ ሳይት 10 ሺሕ 955 የ20/80 ቤቶች በመጠናቀቅ ላይ መሆናቸው ተነገረ

አርትስ 21/02/2011

በአዲስ አበባ የአቃቂ ቃሊቲ ቤቶች ግንባታ ፕሮጀክት ቅርንጫፍ  ፅህፈት ቤት በኮዬ ፈጨ ሳይት 10 ሺህ 955 የ20/80 ቤቶችን ገንብቶ በማጠናቀቅላይ መሆኑን የአዲስ አበባ ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ አስታውቋል ፡፡
በአቃቂ ቃሊቲ ቅርንጫፍ ጽህፈትቤት የኮዬ ፈጨ ሳይት ፕሮጀክት ሥራ አስኪያጅ አቶ ንጉሤ ጸጋዬ  እንዳስታወቁት ቤቶቹን ለመገንባት ገና ከጅምሩየመሰረተ ልማት፣ዲዛይን፣የግብዓት አቅርቦት፣የተሟላ የባለሙያ እጥረትና የዋጋ ግሽፈት ችግሮች ያጋጠመ ቢሆንም እነዚህን ተቋቁመን ግንባታዎቹንከ95 ከመቶ በላይ አድርሰነዋል ብለዋል፡፡
ሥራ አስኪያጁ አያይዘውም ቤቶቹ ሁሉንም ዓይነት የመኖሪያ ቤት ያካተቱ ሲሆን በአጠቃላይ 10ሺሕ 955 የመኖሪያ ቤቶችና የንግድ ሱቆችተገንብተው በመጠናቀቅ ላይ ናቸው ብለዋል፤በዚህ ዓመት የ20/80 ተመዝጋቢዎች የቤት ዕድለኞች እንደሚሆኑ እምነታቸውን ገልጸዋል፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button