SportSports

በሳምንቱ የመጨረሻ ቀናት ተጠባቂ የደርቢ ጨዋታዎች ተከናውነዋል

በሳምንቱ የመጨረሻ ቀናት ተጠባቂ የደርቢ ጨዋታዎች ተከናውነዋል

አርትስ ስፖርት 03/03/2011

በተለያዩ የአለማችን ክፍሎች በተለይ በአውሮፓ ተጠባቂ የእግር ኳስ ግጥሚያዎች ተከናውነዋል፡፡ ሁለቱ የአርጀንቲና ክለቦች ቦካ ጁኒየርስ እና ሪቨርፕሌት በኮፓ ሊበርታዶሬስ የመጀመሪያ የፍፃሜ ጨዋታ፤ የሱፐር ክላሲኮ የደርቢ ግጥሚያቸውን በ ላ ቦምቦኔራ ስታዲየም አካሂደዋል፡፡ ራሞን አቢላ እና ዳርዮ ቤኒዲቶ የባለሜዳዎቹን ቦካን ግብ ከመረብ ሲያገናኙ፤ ሉካስ ፕራቶ እና ካርሎስ ኢዝኬርዶ በራሱ ግብ ላይ የሪቨርን የአቻነት ግብ አስቆጥረው በሁለት አቻ ውጤት ተለያይተዋል፡፡ የመልሱ ጨዋታ ከ12 ቀናት በኋላ በሪቨር ፕሌት ሞኑሜንታል ስታዲየም ይፋለማሉ፡፡ ለ177ኛ ጊዜ በተካሄደው የማንቹሪያን ደርቢ ጨዋታ ደግሞ ትናንት ምሽት በኢቲሀድ በማንችስተር ሲቲ እና በማንችስተር ዩናይትድ መካከል ተካሂዶ፤ ውሀ ሰማያዊዎቹ ከጨዋታ ብልጫ ጋር 3 ለ 1 በሆነ ውጤት ድል አድርገዋል፡፡ የሲቲን የድል ግቦች ዳቪድ ሲልቫ፣ አጎዌየሮ እና ጉንዶሀን ከመረብ ሲያገናኙ፤ የዩናይትድን ከሽንፈት ያልታደገች ግብ አንቶኒ ማርሽያል በፍፁም ቅጣት ምት አስቆጥሯል፡፡ በጀርመን ቡንደስሊጋ የደር ክላሲከር ጨዋታ ደግሞ ቅዳሜ ምሽት በሲግናል ኤዱና ፓርክ ቦርሺያ ዶርትሙንድ በባየርን ሙኒክ ሁለቴ ከመመራት ተነስቶ በ3 ለ 2 ውጤት ረትቷል፡፡ የዶርትሙንድን ጣፋጭ ሶስት ነጥብ ያስገኙ ጎሎች ማርኮ ሪውስ (2)፣ ፓኮ አልካስር ከመረብ ሲያዋህዱ፤ ሮበርት ሉዋንዶውስኪ የባቫርያኑን ሁለት ግቦች አስቆጥሯል፡፡ በጣሊያን ሴሪ ኤ እንደ ደርቢ ደ ኢታሊያ ትልቅ ቦታ የሚሰጠውና የሚቆጠረው ጨዋታ ትናንት በሳን ሲሮ በኤስ ሚላን እና ዩቬንቱስ መካከል ተካሂዶ፤ ዩቬንቱስ በማንዙኪችና ሮናልዶ ጎል 2 ለ 0 ማሸነፍ ችሏል፡፡ በጨዋታው ሂግዌን ፍፁም ቅጣት ምት ያመከነ ሲሆን በቀይ ካርድ ከሜዳ ተሰናብቷል፡፡ በፈረንሳይ ሊግ አንድ ደግሞ በስታዴ ሊዩስ 2ኛ ሞናኮ የሊጉን መሪ ፒ.ኤስ.ጂ አስተናግዶ የ4 ለ 0 ሽንፈት ተከናንቧል፡፡ በጨዋታው ኢዲንሰን ካቫኒ ሀትሪክ ሲሰራ ኔይማር ቀሪዋን አንድ ግብ በማከል የፒ.ኤስ.ጂን መሪነት በ39 ነጥብ አጠናክረዋል፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button