EconomyEthiopiaPolitics

ራይድ የአዲስ አበባ መንገድ ትራንስፖርት ባለስልጣን እየበደለኝ ነው አለ

አርትስ 23/02/2011

 

የሃይብሪድ ዲዛይን ድርጅት ሃሳብ የሆነው እና ራይድ ተብሎ የሚጠራው ታክሲ በከተማዋ የትራንስፖርት አገልገሎትን በመሰጠት የሚታወቅ ሰሆን ስራውን ከጀመረ  በጥቂት አመታት ውስጥ ለበርካታ ዜጎች የስራ እድል  መፍጠሩ ይናገራል፡፡

የድርጅቱ ስራ አስኪያጅ  ወ/ሪት ሳምራዊት  ፍቅሩ  ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እንደተናገሩት፤

በአዲስ ቴክኖሎጂ የትራንሰፖርት ፍሰቱን ለማቃለል አስቦ የሚሰራ ድርጅት መሆኑን  ገልፀው ፤ነግር ግን የአዲስ አበባ መንገድ ትራንስፖርት   ባለስልጣን ከራይድ ድርጅቱ ጋር ውል ገብተው የሚሰሩ መኪኖችን በማሰር እና ህጋዊ ባልሆነ ደረሰኝ በመቅጣት እንግልት  እያደረሱባቸው መሆኑን ገልፀዋል፡፡

የህንንም ቅሬታቸውን ለመስሪያቤቱ በተደጋጋሚ ደብዳቤ ቢያሳውቁም መልስ በለማግኝታችን ቅሬታችንን ለህግ አግባብ እናቀርባለን በማለት ኃላፊዋ ዛሬ ለጋዜጠኞች ጉዳዩን አስመልክቶ በሰጡት መግለጫ  ተናግረዋል  ፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button