Ethiopia

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የየመን ተፋላሚ ሀይሎች ለሰላማዊ መፍትሄ ቅድሚያ እንዲሰጡ ጥሪ አቀረቡ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የየመን ተፋላሚ ሀይሎች ለሰላማዊ መፍትሄ ቅድሚያ እንዲሰጡ ጥሪ አቀረቡ

አርትስ 25/03/2011

 ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በየመን እየተፋለሙ ላሉ ሁሉም አካላት ባስተላለፉት መልእከት፥ ጦርነት ጥፋትን፣ ውድመትን እና መለያየትን የሚያመጣ እንድመሆኑ ሁሉም ተሸናፊ ነው ብለዋል።

 “ጦርነት መሰረታችሁን፣ ግንኙነታችሁን፣ መልካምነታችሁን ያጠፋልያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥ ከጦርነት የሚገኘውም ከጥፋት ውጪ ምንም ነገር እንደሌለ አስታውቀዋል።

በአንድ መሬት ላይ በሚኖር የአንድ ሀገር ህዝብ ላይ እነደዚህ አይነት ነገር ይከሰታል ሲሉም ጠይቀዋል።

ሁሉንም የሀገሪቱን ክፍል በምታወድሙበት ጊዜ የመን ለምን እየተዋጋች ነው የሚለውን ለምን አታሰቡም፤ ከጦርነት እና ግጭት ቋንቋ ይልቅ በንግግር የማመን ቋንቋን ለምን አታስተምሩምብለውም ጠይቀዋል።

ለምን በጠረጴዛ ዙሪያ ቁጭ ብላችሁ መልካሙ ነገር ምንድን ነው በሚለው ላይ አትወያዩም?” ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥ በዚህ መልኩም እንደ አንድ ቤት ህዝብ ያለምንም ደም መፋሰስ እና ጦርነት በነገሮች ላይ አለመግባባት እና መግባባት ትችላላችሁ ብለዋል።

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button